የአባቶቼ አምላክ አላረጀህ በፊቴ ገበታን አዘጋጀህ ጠላቶቼ እያዩ በአይናቸው እራሴን በዘይጥ ቀባህ በፊታቸው ይኸው ምስጋናዬ ለአንተ (2x) ይኸው አምልኮዬ ለአንተ (2x) ይኸው ዝማሬዬ ለአንተ (2x) ይኸው ሙገሳዬ ለአንተ (2x) ይገባሃልና ከእኔ ተቀበል ጌታዬ እግዚአብሔር ከፍ ከፍ በል አቤቱ አምላኬ ሆይ እኔ ማነኝ እስከዚህ ያደረስከኝ ያከበርከኝ እኔ ተገርሜ በፍቅርህ ፊትህ ቀርቤያለሁ ላከብርህ ለውለታህ ምላሽ አጥቻለሁ ያለኝን ልሰጥህ መጥቻለሁ በፊትህ እቀኛለሁ እዘምራለሁ አሸበሽባለሁ እዘምራለሁ ይኸው ሽብሸባዬ ለአንተ (2x) ይኸው ጭብጨባዬ ለአንተ (2x) ይኸው እልልታዬ ለአንተ (2x) ይኸው ጭፈራዬ ለአንተ (2x) ይኸው ውዳሴዬ ለአንተ (2x) ይኸው አክብሮቴ ለአንተ (2x) ይኸው ስግደቴ ለአንተ (2x) ይኸው መገዛቴ ለአንተ (2x) ይገባሃልና ከእኔ ተቀበል ጌታዬ እግዚኣብሔር ከፍ ከፍ በል