እግዚአብሔርን መፍራት ጥበብ ነው የጥበብ ሁሉ መጀመሪያ ከሃጢያት መራቅ ማስተዋል ነው ሃሌሉያ እግዚአብሔርን የሚፈራ እጅግ ብዙ ደስታ ያያል በምድር ላይ እድሜው ይረዝማል በበረከት ይኖራል አይራብም እርሱ ከቶ እግዚኣብሔር ጥጋብ ይሆነዋል በመከራ ዘመን አይሰጋም ጌታ በድል ያሳልፈዋል እንዴት የእግዚኣብሔር ፊት ሃጥያት እሰራለሁኝ ብሎ እግዚአብሔርን ፈርቶ ዮሴፍ ሸሸ ከሃጥያት ኮብልሎ እየጨመረ ቢሄድም ፈተናው ቢሆን ያየለ አምላኩ ሲያስበው ከበር መች ቀረ እንደተጣለ እግዚአብሔርን በመፍራቱ የገባ ከእግዚኣብሔር እይታ በምድር ላይ ቅን ሰው የተባለ ለጠላቱ ያልተረታ እዮብም ታስቦአል በጊዜው በመከራው ሁሉ ታግሶ ከሳሹን አሳፈረለት ጌታ ምርኮውን መልሶ የሰው ልጅ ጥበብን ለማግኘት በዘመኑ ሁሉ ይደክማል ጥበብ ግን እግዚኣብሔር መሆኑን ያወቀ ከርሱ ጋር ይስማማል ዘመኑን በተድላ ሊጨርስ የሚፈልግ እግዚአብሔርን ይፍራ በመውጣት በመግባቱ ሁሉ ያክብረው በየትኛውም ስፍራ እንደቀደሙቱ ሐዋሪያት ላንተ እንደተሰጡ ነቢያት እኔንም ቁምነገረኛ ሰው ለማድረግ ሕይወቴን ቀደሰው ጌታዬ በሰጠኸኝ መክሊት ነግጄበት ቀንና ሌሊት ለመጨረሻው ቀን ሽልማት በድል አዘጋጀኝ የኔ አባት ታማኝ ባሪያ አድርገኝ ጌታዬ እንዲፈጸም ባንተ ደስታዬ ታማኝ ባሪያ አድርገኝ ኢየሱሴ ይህን ትሻለች ካንተ ነፍሴ እንደ ዳዊት በኔ ሕይወት ሰልፉን ቢያበዛብኝም ጠላት መንገዴን ለአንተ አደራ ብዬ እንድጛዝ እርዳኝ አባብዬ ፍጹም ሳልታጣ ከፊትሕ ይፈጸም በሕይወቴ ሃሳብህ አምላኬ በዚህ ክፉ ዘመን እርዳኝ ለቤትህ እንድታመን