Song Lyrics

እሮጣለሁ

Hirut Moges
Lateterahulet Alinorim
ማዳኑን አይቻለሁ ምስክሩ ሆኛለሁ ሥራውን አወራለሁ ጌታዬን አከብራለሁ ከጌታ የተነሳ ነው በህይወት የምኖረው ከኢየሱስ የተነሳ ነው ዛሬም የምዘምረው ምህረቱ ቸርነቱ ለአኔ በዝቶልኝ ነው የትናንቱን እየረሳሁ የዛሬውን ልጨብጥ ወደፊት እዘረጋለሁ በአዲስ መገለጥ ካየሁት ወደሚበልጠው ክብር እሮጣለሁ ካወቅሁት በላይ ለማወቅ እገሰግሳለሁ እሮጣለሁ እስከመጨረሻ (2x) ይህ ነውና የእኔ ድርሻ እጋደላለሁኝ መልካም ገድል ከእጁ ለመውሰድ የፅድቅ አክሊል የእውነትን ቃል በቅንነት እየተናገርኩኝ የምሥራቹን ለፍጥረት እያበሰርኩኝ የማላሳፍር ሠራተኛ ሆኜ በዚች ምድር እተጋለሁኝ እሩጫዬን ልፈጽም ዘወትር መልካሙን ገድል ተጋድዬ ሩጫዬን ስጨርስ ሐይማኖቴንም ጠብቄ ወደ ሀገሬ ስደርስ ጻድቅ ፈራጅ የሆነው ጌታ ያኔ ይሸልመኛል የተዘጋጀልኝን አክሊል ያስረክበኛል መዳኔን አይቻለሁ ምስክሩ ሆኛለሁ ሥራውን አወራለሁ ጌታዬን አከብራለሁ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection