Song Lyrics

አሻፈረኝ

Hirut Moges
Lateterahulet Alinorim
ኢየሱስ ሲጠራኝ እርሱን ተከተልኩኝ (2x) በጣም ረጅም መንገድ ተጉዤ መጣሁኝ (2x) ከእንግዲህ ወደ ኋላ ዞር ብዬ አላይም የመጣ ይምጣ እንጂ ከርሱ አልለይም አሻፈረኝ አሃ ወደኋላ አልመለስም ወስኛለሁ አንዴ ከኢየሱስ ጋር ነኝ አልለየውም የረሳሁት ነገር ከኋላ ቢኖርም ይቅርብኝ ብያለሁ ከኢየሱስ አይበልጥም ለእኔ እንደ ኢየሱስ ማን ይሆንልኛል (2x) በዓለም ካለው ነገር ሁሉ በልጦብኛል (2x) እኔ መርጨዋለሁ ምንም ሳላቅማማ ዛሬ እፎክራለሁ ጠላት እየሰማ የመኖር ትርጉሙ ፍጹም ግራ ገብቶኝ (2x) ሌት ተቀን ስጨነቅ የማደርገው ጠፍቶኝ (2x) ከእለታት አንድ ቀን ኢየሱስ ብቅ አለልኝ ጨልሞ የነበረው ተስፋዬም በራልኝ እንደቀድሞ እንደኔ ግራ የተጋባችሁ ነግቶ ሳለ ቀኑ የጨለመባችሁ ወደ ጌታ ኢየሱስ እኔ ልጋብዛችሁ እና በእርሱ ብርሃን ብርሃን ታያላችሁ እስከዛሬ ጌታ ሰርተሃል ከንግዲህስ ቢሆን ምን ይሳንሃል እኔ በአንተ ተስፋ አልቆርጥም በጠላቴ ዛቻ ከቶ አልናወጥም የኤርትራን ባህር በክንድህ ከፍለሃል ፈረሱን ፈረሰኛውን በባሕር ጥለሃል ዛሬም በእኛ ዘመን ክንድህ ስላልዛለ የጠላትን ስራ ታፈራርሳለህ እስከዛሬ ጌታ ሰርተሃል
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection