ያደረግኸውን ሁሉ ሥራህን እያየሁ እንዴት ዝም እላለሁ (2x) ላመስግን እንጂ አንተን ጌታ ሆይ ከልቤ ቅኔ እየተቀኘሁ (2x) ተመስገን ልበልህ ጌታ ኢየሱስ (2x) ተባረክ ልበልህ ጌታ ኢየሱስ (2x) ተወደስ ልበልህ ጌታ ኢየሱስ (2x) ዛሬም ልበልህ ተመስገን ነገም ልበልህ ተመስገን ሁሌም ልበልህ አምላኬ ተመስገን ጌታ ሆይ እድሜን መቁጠር በአንተ ነው አውቃለሁ በዚህ እደነቃለሁ (2x) ምህረትህ ለኔም በዝቶ ዛሬን አይቻለሁ ላመልክህ ችያለሁ ላከብርህ ችያለሁ አምላኬ አንተን ይዤ ትልቅ ሰው ተባልኩኝ ባንተ ተከበርኩኝ (2x) ያልነበረኝን ሹመት ማዕረግ አግኝቻለሁ እኔም ወግ አየሁኝ (2x) ጥሩ ስም ሰጥተኸኛል መልካም ሰው አርገኸኛል እግዚኣብሔር ውለታ ውለህልኛል ኦ ምስጋናዬን ላብዛብህ (3x) አሜን ምስጋናዬ ይብዛልህ (3x) ጥጋቤነህ ኩራቴ ነህ ትምክህቴ ነህ ልጠግብም ባመልክህ ኢየሱሴ ሌላ ምን ልበልህ ተባረክ ተወደስ ክበር ከፍ በል