Song Lyrics

አንተ እኮ ነህ

Hirut Moges
Lateterahulet Alinorim
ወልዶ አይጥልም ጌታ ያሳድጋል አሳድጎም ለማዕረግ ለወግም ያበቃል (2x) አይቻለሁ በዓይኔ ጌታን በዘመኔ አይቻለሁ በዓይኔ ጥበቃውን በኔ አይቻለሁ በዓይኔ ጌታን በዘመኔ አይቻለሁ በዓይኔ አባት ሆኖኝ ለኔ አይቻለሁ በዓይኔ ጌታን በዘመኔ አይቻለሁ በዓይኔ ታማኝ ሆኖ ለኔ አስቸጋሪ የሆነውን ዓመሌን ችለሃል ከማንም ሰው ይልቅ ለኔ አንተ ተመችተኸኛል አባቴ ሆይ እንዳንተ ያለ ኧረ ማን አለ በፍቅር የሚያባክን ሁሉንም አይቻለሁ አንተ እኮ ነህ ሰብሳቢዬ ኢየሱስዬ አሳዳጊዬ ኢየሱስዬ (4x) መካሪዬ ኢየሱስዬ መጠሪያዬ ኢየሱስዬ አንተ እኮ ነህ መካሪዬ ኢየሱስዬ መጠሪያዬ ኢየሱስዬ አንተ እኮ ነህ ያለ አማካሪ ብቻህን ታምራት ታደርጋለህ ሃጥያተኛን ቀድሰህ ለክብርህ ታቆማለህ ታሪኬ ታድሶልኝ ይኸው እዘምራለሁ አንተ እኮ ነህ መታሰቢያዬ የሱስዬ መታወቂያዬ ኢየሱስዬ (4x) መጀመሪያዬ ኢየሱስዬ መደምደሚያዬ ኢየሱስዬ አንተ እኮ ነህ ጠላት ዙሪያዬን ሲዞር እያገሳ እንደ አንበሳ ሊውጠኝም ሲከጅል መከራዬን ሲያበዛ አንተ ተስፋዬ እኮ ነህ ሁሉም በከፋ ጊዜ ሌላ ረዳት የለኝም ረዳቴ ነህ ኢየሱስዬ አንተ እኮ ነህ ጊዜ ታዳጊዬ ኢየሱስዬ ጠባቂዬ ኢየሱስዬ (4x) ማምለጫዬ ኢየሱስዬ መሸሸጊያዬ ኢየሱስዬ አንተ እኮ ነህ ምንም ነገር በሌለበት ምድረበዳ ላይ ዓይኖቼን በመታመን አንስቼ ወደላይ ስጠራህ የማትዘገይ ፈጥነህ የምትደርስልኝ ለችግር ለጭንቀቴ መፍትሔ የምትሆንልኝ አንተ እኮ ነህ (4x) መታመኛዬ ኢየሱስዬ መጽናኛዬ ኢየሱስዬ መመኪያዬ ኢየሱስዬ መኖሪያዬ ኢየሱስዬ አንተኮ ነህ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection