ዘመኑ ክፉ ነው ክፉ ነው እጅግ ክፉ ነው ደግሞ ኪሣራው ያመዝናል ከትርፉ የዚህ ዘመን ማለፊያ መሸጋገሪያ ድልድይ ኢየሱስ ብቻ ነው የሚያሳርፍ ከሥቃይ አዋጅ አዋጅ ያልሰማችሁ ስሙ ኢየሱስ ያድናል (6x) የመዳን መንገዱ አንዱ ነው እርሱም ኢየሱስ ሌላ መንገድ የለም ወደ ዓብ የሚያደርስ በልጁ ያመነ አይፈረድበትም በሕይወት ይኖራል ለዘለኣለም አይሞትም መድሃኒት ለታጣው ለዓለም አይሞትም መድሃኒት ለታጣው ለዓለም ሁሉ በሽታ መፍትሔ የሚሆን እንቆቅልሽ የሚፈታ ኢየሱስ ብቻ ነው ሕይወትን የሚያለማ ጆሮ ያለው ቢኖር ይህን ዕውነት ይስማ ከሰማየ ሰማያት ፃድቁ አምላክ ወርዶ በምድር ተዋረደ በኛ ፍቅር ተገዶ ሞትን ድል ያረገው የትንሣኤው ባለቤት ጥሪውን ያስተጋባ ለሁሉም በያለበት መሃሪ ነው (2x) ጌታ መሃሪ ነው የማታውቁ ዛሬ እወቁ ኢየሱስ ይቅር ባይ ነው የምሕረት ቃል ያለህ የምሕረት ቃል የሕይወት ቃል ያለህ የሕይወት ቃል ጌታ ሆይ እንዳንተ ማን ይታደጋል? የፍቅር ቃል ያለህ የፍቅር ቃል የምክር ቃል ያለህ የምክር ቃል ጌታ ሆይ እንዳንተ ማን ያሳርፋል? በርሱ ለታመነው ላመነው ጌታ ታማኝ ነው (3x) እርሱ ታማኝ ነው (4x) መሃሪ ነው (2x) ጌታ ይቅር ባይ ነው የማታውቁ ዛሬ እወቁ ኢየሱስ መድሃኒት ነው