ትንሳኤ ታውጆልኝ ሞቴ በሕይወት ተሽሮልኝ ከአንተ ጋር ተወዳጅቼ እዘምራለሁ ተፈትቼ በመስቀል ጣር ወልደኸኝ የአንተ የግል አደረግኸኝ በቤትህ ውስጥ አሳደግኸኝ ልጅህ ሆንኩኝ አባት ሆንኸኝ ውዴ ሆይ (8x) አንተ የእኔ ነህ እኔም የአንተ እኮ ነኝ (4x) እኔ አንድ ነገር አውቃለሁ ይህም እውነት ነው አምናለሁ ውዴ አላማህ በእኔ ላይ ፍቅር ነው ከምንም በላይ ነፍሴ እጅግ ወዳሃለች ሌት ተቀን ውዴ ትላለች ናፍቆቷ ነህ የዘወትር ተማርካለች በአንተ ፍቅር ከአንተ ጋር ጉዳይ አለኝ ሰውማ ምንም ይበለኝ አንተ ነህ ሚስጢረኛዬ የበረሃው ጓደኛዬ በፍቅርህ ተይዣለሁ ሳላይህ እንዴት እውላለሁ ዛሬ ልፈልግ ፊትህን ተናግረህ ልስማ ድምጽህን