አዝ፦ አምንሀለሁ ጌታ አምንሀለሁ አምንሀለሁ ኢየሱስ አምንሀለሁ (2x) ሠማይ ምድር ያልፍል ቃሌ ግን አያልፍም ከአፌ የወጣዉ ቃል እንዲሁ አይመለስም ብለህ እንደተናገርህ ቃልህን ፈጸምከዉ ኮራሁብህ ኢየሱስአንተ በሰራኸዉ ብታደርግ ልክ ብታፈርስ ልክ የማትሣሣት ፍፁም የሆንክ አንተ ሥራ እንጂ ቃልህን ላክና ሚከለክልህ የቱ ነው ጀግና ከአንተ ወዲያ ጀግና አዝ፦ አምንሀለሁ ጌታ አምንሀለሁ አምንሀለሁ ኢየሱስ አምንሀለሁ (2x) ሁኔታ ሚሰብከኝ ሚያስፈራ ነገር ነው የሚታየው ሁሉ እጅግ አስደንጋጭ ነው ቃልህ ትዝ ሲለኝ አይዞህ ነው የሚለኝ እንዳልፈራ እንዳልዝል ነው የሚያስታውስኝ መች በሰው ስሌት በአዋቂ መላ ሆኖ ያውቅና የአንተ እኮ ሌላ ዛሬ ርሃብ ሆኖ ነገ ጥጋብ ነው ሥትል አምናለሁ ሁሉ የአንተ ነው ሁሉ በእጅህ ነው አዝ፦ አምንሀለሁ ጌታ አምንሀለሁ አምንሀለሁ ኢየሱስ አምንሀለሁ (2x) ውጣ ያልከኝ አንተ እንሆ ምድሪቷ ሥሜን አውጅባት በርዝመት ስፋቱዋ አብሬህ እሆናለሁ እስከ መጨረሻው ሥትል ተቀበልኩኽ ካሳብህ ተስማማሁ እንደ አባቶቼ በአንተ ታምኜ እራሴን ክጄ በዓለም ጨክኜ ከኖሩስ አይቀር እንዲህ ነው ኑሮ አንተን አክብሮ ደሞ አስከብሮ (2x) ዛሬም ተመለክ አንተ አምላክ ነህ ዛሬም ተደነቅ አንተ ድንቅ ንህ ዛሬም ተወደስ አንተ ጀግና ነህ ዛሬም ተሞገስ አንተ ልዩ ነህ ሲያንሥህ ነው ጭብጨባ (4x) ሲያንሥህ ነው ዕልልታ (4x)