ማስተዋልህ በሊቅ አትመረመርም እግዚአብሔር ታላቅ ነህ ማንም አላየህም በላይ በከፍታ በክብር ትኖራለህ በበረከትህም ምድርን ታጠግባለህ ባለጠግነትህ አይጐድልም ይፈቃል ይፈሳል ዘላለም (2x) አዝ፦ ሃሌሉያ ክብር ይገባሀልና አምሣያ የሌለህ ሁሉን ቻይ ነህና (2x) የፊትህ ብርህን ከፀሐይ ይደምቃል ሰባቱን ከዋክብት በእጆችህ ይዘሀል አይኖችህ እንደ እሣት ነበልባሎች ናቸው የራስህም ፀጉር ከነጭም ነጭ ነው ማን መቆም ይችላል ካንተ ጋር አይቶ ነፍስ ማን ይቀርለታል (2x) አዝ፦ ሃሌሉያ ክብር ይገባሀልና አምሣያ የሌለህ ሁሉን ቻይ ነህና (2x) መላዕክት በፍርሀት ወድቀው ይሰግዱልሀል ያምልኮአቸው ሽታ ቤትህን ሞልቶታል ክብርና ውዳሴ ምስጋና ይገባሀል እያሉ እራቱ እንስሶች ያከብሩሀል ሽማግሌዎች ወድቀው የሰግዱልሀል በፈቃድህ ሁሉን ፈጥረሀል እያሉ ክብራቸውን ይሰጡሀል አዝ፦ ሃሌሉያ ክብር ይገባሀልና አምሣያ የሌለህ ሁሉን ቻይ ነህና (2x)