Song Lyrics

ማረኝ

እጅህ አላጠረም ከመስራት ድምጽህ አልደከምም ከመጥራት ይልቅ በበደሌ ያሳዘንኩህ እኔ ማስተዋል ያቃተኝ በቃልህ ስትነግረኝ ስለዚህ አምልኮዬ ሆነ አንካሳ አንዳች ጠብ አይልም በስምህ ብወቅድ ብነሳ አዝ፦ ማረኝ ማረኝ ጌታ ማረኝ (2x) ማረኝ ማረኝ ኢየሱስ ማረኝ የእኔ ነው ጠብና ክርክር ከአንተ ይልቅ መፈለግ የራስ ክብር የተጋረደ ነው በእኔ ያለው ብርሀን እንቅፋት ሆኛለሁ ስለ ሌሎች መዳን ኑሮዬ ምልክት የለውም የአንተነት ሥጋዬ በርትቶአል መንፈሴ ግን ደክሟል አዝ፦ ማረኝ ማረኝ ጌታ ማረኝ (2x) ማረኝ ማረኝ ኢየሱስ ማረኝ አይታዘዝ ልቤ ጠማማ ምላሴ አይደንግጥ ሲያማ ወገኑን የማይወድ ቂመኛ ልብ ያለው ትዕቢት የተሞላ ከኔ ሌላ ማነው የቀደሙወን ፍቅር ከጣልኩት በጣም ቆይቻለሁ ሰው ሲያየኝ የቆምኩኝ ብመስልም እኔስ ወድቂያለሁ አዝ፦ ማረኝ ማረኝ ጌታ ማረኝ (2x) ማረኝ ማረኝ ኢየሱስ ማረኝ ሁለንተናዬ ግልጽ በፊትህ አንዳች እንኳን የለ ማልነግርህ ከእግርህ ስር ወድቃለሁ እስከነህ ኃጢያቴ በደምህ ታመኜ ዳግም ለመንፃቴ እባህክ ስለ ስምህ ብለህ ራራልኝ በቀራንዮ መስቀል በከፈልከው ዋጋ አስበኝ አዝ፦ ማረኝ ማረኝ ጌታ ማረኝ (2x) ማረኝ ማረኝ ኢየሱስ ማረኝ አንደገና እንደ አዲስ ሃይልን እሞላለሁ አዝ፡- በንስሀ ፍሬያማ ህይወት እኖራለሁ ፀጋህ ይበዛለኛል ቃልህ እበላለሁ መንፈስህን ጠጥቼ የልብህ ሰው እሆናለሁ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection