Song Lyrics

ክንደ ብርቱ

አበቃ አከተመ አይሆንም በተባለበት የጌታ ስም ሲጠራ ሁሉ ይዘራል ህይወት ያለአንዳች እርዳታ ብቻውን ድንቅን አድርጐ ልጆቹን ያሣርፋል በሀይሉ ተገለጦ ታላቅነቱ አይወሰን ከ እስከ አይባልም ብቻ እርሱ ይስራ እንጂ ማንም ፊቱ አይቆምም (2x) አዝ፦ ጌታችን ክንደብርቱ ነው (3x) የለም ሚገዳደረው አርሱ ብርቱ ነው ኢየሱስ አሸናፊ ነው (3x) ማነው የሚቋቋመው አሸናፊ ነው (2x) ጽኑ ግንብ በጠላት ፊት የማይደፈር መከታ ከክፋት ከሰይጣን እጅ የሚከልል ጌታ ነው እኛ ምናመልከው ሀይለኛና ባለስልጣን ተጠግተነው አርፈናል መደገፊያ ሆኖልን ጥበቃው እጅግ ያስደንቃል ልጆቹን ያሳርፋል ሀይሉም ከቶ አይደክምም በሰልፍ ይበረታል (2x) አዝ፦ ጌታችን ክንደብርቱ ነው (3x) የለም ሚገዳደረው አርሱ ብርቱ ነው ኢየሱስ አሸናፊ ነው (3x) ማነው የሚቋቋመው አሸናፊ ነው (2x) ጌታ ከርሱ ጋር የሆነ ኽረ ሌላ ምን ያሻዋል ከክንፎቹ በታች ሆኖ ተማምኖ ይኖራል በክፉ ቀን አይሰጋም አምላኩ ይታደገዋል ከረግረግ ከጭቃ አውጥቶ በአለት ያቆመዋል ዛሬም ይህ ጌታ ከእኛ ጋራ ካለ ምንደነው የሚያስፈራን በእርሱ እየተማመንን በድል እንሄዳለን (2x) አዝ፦ ጌታችን ክንደብርቱ ነው (3x) የለም ሚገዳደረው አርሱ ብርቱ ነው ኢየሱስ አሸናፊ ነው (3x) ማነው የሚቋቋመው አሸናፊ ነው (2x) ከጌታ የተነሳ በህይወት መኖር ችለናል ካስጨናቂዎቻችን ሁሉ በእርሱ አርፈናል ማዳኑን የክንዱን ብርታት ባይናችን አሣይቶናል ስለዚህም ልናከብረው ወደ እርሱ መጥተናል ለክበሩ እንዘምራለን እናመሰግነዋለን ጌታ ስለሚገባው እናመልከዋለን (2x) ምስጋና ለርሱ ይገባዋል (3x) ሌላ ምን ይሰጠዋል ለርሱ ይገባዋል (4x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection