Song Lyrics

ትመቸኛለህ

ትመቸኛለህ ጌታዬ ትመቸኛለህ ኢየሱስ (2x) ከእናት ማህፀን እስከ ሽመግልና ድረስ ምተሸከም አምላክ ቃልህን ማታፈርስ ፍፁም ነው ፍቅርህ የሱስ ያለ እንከን የሆነ የኽው ተስፋ ያለው ሠው አረከኝ ህይወቴ ሰከነ (2x) አዝ፦ ትመቸኛለህ ጌታዬ ትመቸኛለህ ኢየሱስ (4x) በዓለም ሣለሁኝ ከአለም ተለይቼ ልኖር ከንቱ እንደሆነ አውቄ የዚህች ምድር ክብር ስደክም ስበረታ በህይወት መንገድ ላይ ክንዶች ያሣረፈኝ የደላኝ የለም ካንተ በላይ አዝ፦ ትመቸኛለህ ጌታዬ ትመቸኛለህ ኢየሱስ (4x) ሳልወድ ወይም ሣልሮጥ ምህረትን አግኝቻለሁ ነፍሴን አርክተሀት ልዩ ሰው ሆኜአለሁ መቅበዝበዜ አሣዝኖህ ፈልገህ አግኝተኽኝ ከቶ እንዳይጠማኝ የሕይወትን ውሃ አጠጣኽኝ አዝ፦ ትመቸኛለህ ጌታዬ ትመቸኛለህ ኢየሱስ (4x) የልቤ ፍሰሀ አምላኬና አባቴ ለኔ መቼም የማትተወኝ ማገኝህ ከጐኔ ምላሴ ሲያከብርህ በሚችለው ሁሉ የአካል ክፍሎቼ ተባብረው በደስታ ያመልካሉ አዝ፦ ትመቸኛለህ ጌታዬ ትመቸኛለህ ኢየሱስ (8x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection