የሳተ ይመለስ የለም ወይ ከግድፈቱ የወደቀስ ይጠገን የለም ወይ ከስብራቱ አይኖቹን ሲያቀና በተስፋ ወደአንተ ሲማፀን ምህረትን እየወተወተ አይችልም መጨከን አንጀትህ የአባትነትህ አጥበህ ታነፃለህ አንተ ፍቅር ነህ ይሄንን ላውራልህ አዝ፦ ብደክም ወድቄ እንዳልቀር ፀጋህ ብዙ ነው ያግዘኛል ምህረትህ ከቁጣ ይፈጥናል እንድኖር ምክንያት ሆኖኛል አልመካም መች ቆሜ ባቅሜ ባትረዳኝ ሆነህ አጠገቤ ከጐኔ (2x) በጨለማ ብቀመጥ ብርሀኔ ነህ የሀጢያት ሸክም ቢያጐብጠኝም ታቀናኛለህ ተስፋዬ ይቅርታ መጽናኛዬም ፊትህ ነው ስለቸርነትህ ብቻ ነው ምኖረው ሲሰማኝ መኖርህ ሳስተውል መገኘትህን መንፈሴ ያንስራራል ነቅቶ ያዳምጥሀል ጌታዬና አምላኬ ይልሃል አዝ፦ ብደክም ወድቄ እንዳልቀር ፀጋህ ብዙ ነው ያግዘኛል ምህረትህ ከቁጣ ይፈጥናል እንድኖር ምክንያት ሆኖኛል አልመካም መች ቆሜ ባቅሜ ባትረዳኝ ሆነህ አጠገቤ ከጐኔ (2x) ጉስቁልናዬን ስታይ አዘንክልኝ እራርተህ እጅህን ዘረጋህ አቅፍህ ልታነሳኝ ግድ የሚልህ ለኔ መጥፋቴን ማትወደው ፊትህ ለኔ በራ በደሌንም ተውከው እንደባሪያ መሆን ሳያንሰኝ አንተ ግን ልጅ አልከኝ እራሴን ልስጥህ ዝቅ ልበልልህ ላንተው ኖሬ ላንተው ልሙትልህ አዝ፦ ብደክም ወድቄ እንዳልቀር ፀጋህ ብዙ ነው ያግዘኛል ምህረትህ ከቁጣ ይፈጥናል እንድኖር ምክንያት ሆኖኛል አልመካም መች ቆሜ ባቅሜ ባትረዳኝ ሆነህ አጠገቤ ከጐኔ (2x) በምህረትህ ብዛት ቤትህ እገባለሁ (2x) ስለምህረትህ ጌታ አመልክሃለሁ (2x) በፊትህ ሞገስ ያገኘሁት አይደለም በእራሴ ያቆሙኩት የፅድቅ የሥራ መልካም ነገር ምህረትህ ድፍረት ሆኖልኝ ነው የፀጋህ ማስቻሉ በዝቶልኝ ነው ስምህን ላክብረው (2x)