Song Lyrics

ላመስግነህ

የህይወቴ እስትንፋስ በእጅህ መዳፍ ውስጥ ነው ያለው ያለ አንተ መኖር አልችልም በእርግጥ ሞቼ እቀራለሁ ህያውነቴ ባንተ ነው በነፍሴ ጌታ ለዘላለም ላመስግንህ ላዚም በእልልታ (2x) ልባርክህ ልባርክህ ላምልክህ ላምልክህ (2x) አዝ፦ በአዲስ በአዲስ ቅኔ እቀኝልሀለሁ እኔ በአዲስ በአዲስ ዜማ ድምጼ ለአንተ ይሰማ (2x) ከልቤ በሙሉ ሀይሌ (2x) አመሰግንሀለሁ ክብርን ለአንተ እሰጣለሁ (2x) ኢየሱስ (2x) ኢየሱስ (4x) አምላኬ አንተ ለእኔ መታመኛዬ አለቴ ደስታዬ አንተን ሳስብ ነው በእርግጥ ማረፍ መርካቴ ስለዚህ አንተን ላምልክህ ላውራ ክብርህን የዝማሬ ጽምፅ ይሰማ ላሸብሽብልህ (2x) ከፍ ላርግህ ከፍ ላርግህ ላውድስህ ላወድስህ (2x) አዝ፦ በአዲስ በአዲስ ቅኔ እቀኝልሀለሁ እኔ በአዲስ በአዲስ ዜማ ድምጼ ለአንተ ይሰማ (2x) ከልቤ በሙሉ ሀይሌ (2x) አመሰግንሀለሁ ክብርን ለአንተ እሰጣለሁ (2x) ኢየሱስ (2x) ኢየሱስ (4x) እንዳንተ የሚሆን ለእኔ አላገኘሁምና ከእናትም ከአባት ከወዳጅ በልጠህብኛልና አምላኬ መድሀኒቴ ነህ ለእኔ ፈዋሼ በአምላኮ አንተን ማክበር ነው ምላሼ (2x) ላመስግንህ ላመስግንህ ላሞጋግስህ ላሞጋግስህ (2x) አዝ፦ በአዲስ በአዲስ ቅኔ እቀኝልሀለሁ እኔ በአዲስ በአዲስ ዜማ ድምጼ ለአንተ ይሰማ (2x) ከልቤ በሙሉ ሀይሌ (2x) አመሰግንሀለሁ ክብርን ለአንተ እሰጣለሁ (2x) ኢየሱስ (2x) ማፍቀሬን ለአንተ ያለኝን ጥልቅ የሆነ መውደዴን እገልፃለሁ ለስምህ ክብር በማቅረብ መስዋዕቴን ደጋግሜ አመልክሃለሁ ይህም ያንስሀል ያለምንም ዋጋ እንዲሁ አድነኽኛል (2x) ልቀኝልህ ልቀኝልህ ላክብርህ ላክብርህ (2x) አዝ፦ በአዲስ በአዲስ ቅኔ እቀኝልሀለሁ እኔ በአዲስ በአዲስ ዜማ ድምጼ ለአንተ ይሰማ (2x) ከልቤ በሙሉ ሀይሌ (2x) አመሰግንሀለሁ ክብርን ለአንተ እሰጣለሁ (2x) ኢየሱስ (2x) ኢየሱስ (4x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection