Song Lyrics

አየሁ

አዝ፦ አየሁ እኔስ እኔስ አየሁ በዚህች እድሜ ስንቱን አየሁ በዙፋኑ ፀንቶ ያለው እግዚአብሔር ግን ሁሌም ያው ነው (2x) እግዚአብሔር ግን ሁሌም ያው ነው (6x) ትላንት ሲታይ ማይደፈር ሲባል ዛሬ አይን ላፈር አንቱ መባል ትላንት አንሶት ዛሬ አንተነት ሲበዛበት ሰው ወዶ የሾመውን ሰው ወዶ ይሸረዋል (2x) ከእኛ እግዚአብሔር ጋር ግን ማን ይስተካከላል ከዘለአለምም እስከ ዘለአለም (2x) ነው መንግስቱ ጽኑ የሚመስለው የለም አዝ፦ ህያው ነው እግዚአብሔር ህያው ነው (2x) ጌታ ነው ኢየሱስ ጌታ ነው (2x) አንድ ሺ ቀን እንደአንድ ቀን አንድ ቀንም አንደአንድ ሺ ሁሌ ጌታ በዘመናት ፈጣሪያቸው ለእለታት በጊዜ አይገደብ እርሱ እግዚአብሐር ነው (2x) አመቶቹ አያልቁ ጸንቶ የሚኖር ነው ያሳልፋል እንጂ እርሱ አንደው አያልፍም (2x) ተላንትናም ዛሬም ያው ነው ለዘላለም አዝ፦ ህያው ነው እግዚአብሔር ህያው ነው (2x) ጌታ ነው ኢየሱስ ጌታ ነው (2x) አልፋ ኦሜጋ እርሱ እኮ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection