አሃ አሃ አዝ፦ ለድል እንጂ ለሽንፈት እኔ አልተጠራሁም (2x) ጌታዬ ሲጠራኝ ከዚያ ከጨለማ እባብና ጊንጡን እንድረግጥ ነውና ኢየሱስ ሲያወጣኝ ከዚያ ከጨለማ እባብና ጊንጡን እንድረግጥ ነውና በማይመች ነገር የሚመቸው ጌታ አሃሃ ከእኔ ጋር ስላለ በድፍረት እላለሁ ኢየሱስ ነው ጌታ (2x) ድል አድራጊዉ ጌታ ድል ያንተ ነዉ ብሏል ጠላቴ ሆይ ስማ ድል መንሳትስ የታል አሸናፊው ጌታ ድል ያንተ ነው ብሏል ጠላቴ ሆይ ስማ ድል መንሳትስ የታል አዝ፦ ለድል እንጂ ለሽንፈት እኔ አልተጠራሁም (2x) ጌታዬ ሲጠራኝ ከዚያ ከጨለማ እባብና ጊንጡን እንድረግጥ ነውና ኢየሱስ ሲያወጣኝ ከዚያ ከጨለማ እባብና ጊንጡን እንድረግጥ ነውና የምሞትበት ተሽሯል አዋጁ ትዕዛዝ አውጥቷል ታሪክን ለዋጩ መስንቆዬም ይውረድ ከተሰቀለበት ለአሸናፊው ጌታ መዝሙር ይዜምበት በአዲስ ምስጋና በዕልልታ ሆታ ፊቱ እገባለሁ ከፍ ይበል ጌታ ይኽው ሽብሸባ ይኽው ስግደቴ ድልን ስለሰጠኝ ለመድሃኒቴ ለሆነኝ ጉልበቴ ይኽው ስግደቴ ይኽው እኔነቴ አዝ፦ ይኽው ተቀበለው ጌታ ይኽው ላንተ ያለኝ ዕልልታ ይኽው ተቀበለው አባ ይኽው ላንተ ያለኝ ጥብጨባ ይኽው ይኽው አምልኮው ይኽው ይኽው ይኽው ዝማሬዉ ይኽው ይኽው ይኽው ሽብሸባው ይኽው ይኽው ይኽው ዕልልታው ይኽው ጨለማዬ በራ የፅድቅ ፀሃይ ወጣ የመጐብኘት ዘመን ይኽው ለእኔ መጣ እንዲሁ አልቀረሁም በመድረ በዳ ላይ ዘንበለ ብሎልኛል ጌታዬ ከሰማይ ስሙ ከፍ ይበል ይወደስ ይግነን የአምልኮ ሽታ ቤቱን የሙላልኝ በጠላቴ ላይ ድልን ለሰጠኝ ለዚህ ለጌታ እልልታ አለኝ ዝማሬ አለኝ ሽብሸባ አለኝ አምልኮ አለኝ አዝ፦ ይኽው ተቀበለው ጌታ ይኽው ላንተ ያለኝ ዕልልታ ይኽው ተቀበለው አባ ይኽው ላንተ ያለኝ ጥብጨባ ይኽው ይኽው አምልኮው ይኽው ይኽው ይኽው ዝማሬዉ ይኽው ይኽው ይኽው ሽብሸባው ይኽው ይኽው ይኽው ዕልልታው ይኽው