በመንገድህ አግኘኝ ጌታ እንደ ሀሳብህ ለትጐበኘኝ ስትመጣ እንዳልጠፋ ከፊትህ ፀጋህን አብዛልኝ ኢየሱስ በሕይወቴ መንፈስህ ያግዘኝ ይጽና መሰረቴ (2x) አዝ፦ ምህረትን ትወዳለህና ብርታትን ትሰጣለህና እኔም ልታሰብ ጌታ ኃይል ይብዛልኝ ልበርታ ኑሮዬ አንተን ይምሰልህ ከፍ ያድርግህ ያክብርህ አሜን ስለ እኔ ነፍስህን ልትሰጥ አልሰሰትክምና እዳዬን ሁሉ ልትከፍል ተችሎሀልና እኔም ለመውደድህ ልሁን እንደልብህ አንተን መፍራት ሙላኝ ዝቅ ልበልልህ (2x) አዝ፦ ምህረትን ትወዳለህና ብርታትን ትሰጣለህና እኔም ልታሰብ ጌታ ኃይል ይብዛልኝ ልበርታ ኑሮዬ አንተን ይምሰልህ ከፍ ያድርግህ ያክብርህ አሜን በመቅደስህ ቀድሰኝ በእሣትህ አንጥረኝ የማትወደው ከእኔ ይቆረጥ እንዳሻህ አበጃጀኝ ለእኔም የሻለኛል በእጅህ መቀረፁ ኋላ ሞልቶ ይፈሣል ከአንተ በረከቱ (2x) አዝ፦ ምህረትን ትወዳለህና ብርታትን ትሰጣለህና እኔም ልታሰብ ጌታ ኃይል ይብዛልኝ ልበርታ ኑሮዬ አንተን ይምሰልህ ከፍ ያድርግህ ያክብርህ አሜን ድንጋዩ ልብ ከእኔ ይውጣ ስጋ ይሁንልኝ የቀናውን መንፈስህን በውስጤ አድስልኝ ክርስቲያን ከተባልኩ በአንተ ከተጠራሁ እንደ ሀሳብህ ኖሬ ማለፍን እሻለሁ (2x) አዝ፦ ምህረትን ትወዳለህና ብርታትን ትሰጣለህና እኔም ልታሰብ ጌታ ኃይል ይብዛልኝ ልበርታ ኑሮዬ አንተን ይምሰልህ ከፍ ያድርግህ ያክብርህ አሜን (2x)