Song Lyrics

ስለአምላክነትህ

አዝ፦ ስለ አምላክነትህ ስለ ጌትነትህ ስለ እጆችህ ስራ ባወራው ባወራ አያልቅ የአንተ ሥራ (2x) አያልቅ የአንተ ስራ (4x) ሰባቱን ከዋክብት ኦርዬንን የሰራ ጨለማውን ንጋት ብርሀን የሚያበራ ቀኑን አጨልሞ ሌሊት የሚያደርገው ስራው እንዲህ ያማረው ስሙ እግዚአብሔር ነዉ (2x) አዝ፦ ስለ አምላክነትህ ስለ ጌትነትህ ስለ እጆችህ ስራ ባወራው ባወራ አያልቅ የአንተ ሥራ (2x) አያልቅ የአንተ ስራ (4x) ውሆችን በእፍኙ የሰፈረ ጌታ ሰማይንም ደግም በስንዝር የለካ ኽረ እግዚአብሔርን የአማከረው ማነው ማስተዋሉ ረቂቅ ኃይሉ እጅግ ብዙ ነው (2x) አዝ፦ ስለ አምላክነትህ ስለ ጌትነትህ ስለ እጆችህ ስራ ባወራው ባወራ አያልቅ የአንተ ሥራ (2x) አያልቅ የአንተ ስራ (4x) በዓመታት መሀል ስራን ትሰራለህ ሁኔታ አያግድህ ከሁኔታ በላይ ነህ አቤት ይሄ ጌታ እኔ የማመልከው ለዘላለም ነዋሪ መለወጥ የማያውቁው (2x) ስለዚህ ላምልከው በሀሴት ውሰጥ ሆኜ የማይለወጠውን ስላገኘች ነፍሴ ከቤቱ በረከት ስለረካች ነፍሴ (2x) ከእርሱ ሌላ አልፈልግም እርሱ ለእኔ ምኞቴ ነው ርሀቤም ጥማቴም የሆነው ከእርሱ ሌላ አልፈልግም እርሱ ለእኔ መሻቴ ነው ርሀቤም ጥማቴም የሆነው ርሀቤም ጥማቴም የሆነው (፲6x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection