ኢየሱሴ/2/ ብዬ ስምህን ስጠራ ይኸው ሸለቆዬ በውኃ ሞላ/3/ የኔ ጌታ/2/ ብዬ ስምህን ስጠራ ባዶ ማድጋዬ በዘይትህ ሞላ/3/ ኧረ ጌታዬ ስምህን ጠርቶ ማን አፍሮ ያውቃል ኧረ ኢየሱሴ ስምህን ጠርቶ ማን አፍሮ ያውቃል የመጽናናት ዘመን መጣልኝ እሰይ እኔም ተራ ደርሶኛል የመጎብኘት ዘመን መጣልኝ እሰይ እኔም ተራ ደርሶኛል አይቻለሁ የተዋረደውን ታከብራለህ/3 አይቻለሁ ካመድ ከትቢያ ታነሳለህ/3 እኔን ከትቢያ አንስተኸኝ ወርደቴን በክብር ለወጥክልኝ ክበር በአንተ ከብሬአለሁ 2 ከዚህስ ሌላ ምን እሻለሁ ታሪኬ ባንተ ተለውጧል ይኸው ሰው ሆኜ አምሮብኛል የኔ መመኪያ ኢየሱሴ 2 ባንተ አርፋልኛለች ነፍሴ ብርሃኔና መድኃኒቴ መተማመኛዬ ዓለቴ ባንተ ጥላ ስር ተከልዬ 2 እኖራለሁ ተደላድዬ አንተ ብርቱ አንተ ኃያል አንተ ገናና ማደሪያህን ይሙላው የኔ ምስጋና/4 አንተ ጌታ አንተ ኃያል አንተ ገናና መቅደስህን ይሙላው የኔ እልልታ/4