Song Lyrics

ፈውስህን

እንደ በርጤሜዎስ እኔም እጠራሃለሁ የዳዊት ልጅ ማረኝ ማረኝ እልሃለሁ ጌታ ኢየሱስ እባክህን አትለፈኝ በዚህ ሰዓት ፈውስ ካንተ ይሁንልኝ ፈውስህን /3/ እጠብቃለሁ ለመፈወስ ጓጉቻለሁ ማረኝ ማረኝ እልሃለሁ ማረኝ ማረኝ እልሃለሁ ደስታዬ ጠፍቶ ተተክቶ በትካዜ ቁስሌም ሁሉ ተመልሶ አመረቀዘ በዚህ ስቃይ እስከ መቼ አለቅሳለሁ ተንበርክኬ ለመፈወስ አነባለሁ ሸክሜ በዝቶ እንደምታይ ጎብጫለሁ ከድካም ልትፈታኝ ችሎታህን አውቀዋለሁ በፊቴ ያለውን ጨለማዬን ግፈፍልኝ የታወሩትን አይኖቼንም ክፈትልኝ እስከ ዛሬ ያነከስኩት እስኪ ይብቃኝ ሽባነቴ ተተርትሮ አስዘልለኝ መድኃኒቴ ህመማቴን ውሰድና ፈውሰኸኝ አፌን ሙላው በምስጋና
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection