Song Lyrics

ለታላቅነትህ

ለታላቅነትህ ዝማሬ ይሰማ ለተቀደሰው ስምህ የምስጋና ዜማ በክብር በግርማ ልዕልናን ልበስ እንበልህ እኛም ይሁን ላንተ ሞገስ ሞገስህን በቋንቋ ማወደስ ለፍቅርህ መግለጫ ቃል ስለሚያንስ ምስጋናችን ደርሶ ከዙፋንህ ይኸው የዝማሬ ቃላችን ይጣፍጥህ ዓይን ሁሉ ተስፋ ያደርግሃል ማዳን ቸርነት ምህረትህን ይሻል የምስጋናን መስዋዕት ላቀረበው ሁሉን ትሰጣለህ ችሮታህ ብዙ ነው የደከመን በርግጥ ታያለህ የተጠማውንም ታረካለህ ለዚህ ስራህ ምን ትቀበላለህ በመዝሙር ውዳሴ ትመሰገናለህ ምስጋና ላንተ ምስጋና ከአማልክት ሁሉ በላይ ነህና ከሰማያት ሰማይ ከፍ ብለህ በፍጥረት ሁሉ አፍ ትመሰገናለህ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection