አምላካችን ይህ ነው ጠብቀነዋል እግዚአብሔር ይህ ነው ተስፋ አድርገነዋል ማዳኑን ዓይተናል በርሱ ደስ ይለናል |2| በምድረ በዳ ውስጥ ጭው ባለው በረሃ እንጀራ እንዳይርበን እንዳይጠማን ውኃ የሰማይን መና እጁ መግቦናል አለቱን ሰንጥቆ ውኃ ጠጥተናል ይመስገን እዚህ ደርሰናል |4| ቀኑን በደመና ሌሊት በእሣት አምድ እርሱ እየመራን ከፊታችን ሲሄድ ዮርዳኖስን ከፍሎ በድል አሻግሮናል እባብና ጊንጡን በስሙ ረግጠናል ይመስገን እዚህ ደርሰናል |4| ከፊታችን ያለው የኢያሪኮ ቅጥር እንደተናገረን በእምነት ስንዞር ተደምስሶ ወድቆ ምድሪቱን ወርሰናል የጌታችንን ኃይል በዓይናችን አይተናል ይመስገን እዚህ ደርሰናል |4| አቻምናን አለፍነው እርሱን ተደግፈን አምናንም ተሻገርን በእጆቹ ተይዘን ዛሬን በእርሱ ታምነን ነገን ሰጥተነዋል በአዲስ ራእይ ብርሃን አስረክበነዋል እዚህ ያደረሰን ይመስገን |4|