ከውርደት ስፍራ ከትቢያ አንስተህ በሠልፉ ሜዳ ፊት ለፊት ቀድመህ ሕዝብህን በኃይል ስትመራ አየሁህ አቤቱ አምላኬ አንተ ታላቅ ነህ አቤት እንዴት ልዩ ነህ እንዴት ድንቅ ነህ እንደ ሰማሁት በዓይኖቼ አየሁህ ተመስገን ለውለታህ ምላሽ ሌላ ምን አለኝ ተመስገን ተንቆ የነበር ታላቅ ሕዝብ ሆኖ ሥራህ በእርሱ ላይ ታይቶ እጅግ ገኖ በእምነት ሲራመድ በጠላቱ ላይ አንተንም አየሁ ከሁሉ በላይ በመከራ ውስጥ የታመነብህ ስምህን ይዞ ያላፈረብህ ሕዝብህን አየሁት የድሉ ለታ ክብርህን ሲያውጅ ሲያዜም በልልታ ራሴንም ሳስብ ያንተው መሆኔን ፀንቼ ብቆይ የማገኘውን እጅግ ደስ አለኝ በአባትነትህ ስላለኝ ተስፋም አመሰገንኩህ