ምህረት ቸርነትህ እጅግ በዝልቶኝ እዚህ ደርሻለሁ እየመራኸኝ ምህረት ቸርነትህ እጅግ በዝልቶኝ ይኸው ዛሬም አለሁ ተሸክመኸኝ ከፊት ከኋላዬ ጠላትም ሲከበኝ መረቡን ዘርግቶ ጠላልፎ ሊጥለኝ ከዙፋንህ ሆነህ ስለተመለከትክ መንፈስህን ልከህ ወጥመዱን ሰባበርክ በመከራዬ ቀን ድንኳንህ ሰወርከኝ ጩኸቴንም ሰምተህ በጉያህ ሸሸከኝ የነፍሴ ጠባቂ መከታዬ ሆንከኝ ታሪኬን ለውጠህ ለክብርህ አቆምከኝ በኅዘኔ ፈንታ ደሰታን የሞላኸኝ ሕይወቴን ለውጠህ እኔን ሰው ያረከኝ ከብዶኝ የነበረውን ቀንበር ጥለህልኝ የዘላለም አምባ መኖሪያ ሆንክልኝ ምህረት ቸርነትህን እንዳወራ ወደህ ክብርህን ገለጥከው በድካሜ አልፈህ ላረክልኝ ሁሉ ምን እመልሳለሁ በፊትህ ወድቄ እሰግድልሃለሁ