Song Lyrics

ጌታችን ሆይ

ጌታችን ሆይ ስምህ በምድር ሁሉ ተመሰገነ/2/ ታላቅነትህ ዝናህ ገነነ ፣ ኃያልነትህ ክብርህ ገነነ ጌታችን ሆይ ሰምህ በምድር ሁሉ ተመሰገነ ተራሮች ጨሱ ኮረብቶች ጋዩ አሕዛብ ቀለጡ ማዳንህን አዩ ምላስም ሁሉ አንተን ባረከ ጉልበት ለስምህ ተንበረከከ ኃያላን ሁሉ ብርታት ከዳቸው ዝለው ወደቁ ላላ ትጥቃቸው አንተ ብቻ ነህ ጸንተህ የምትኖር ታላቅነትህ ታውቆ በምድር ጠላቶችህ እንደ ሰም ቀለጡ የሚጠሉህም እንደ ጢስ በነኑ ጠንካራው ዓለት ተሰነጠቀ ገናናነትህ በምድር ታወቀ ፍጥረታት ስምህን አመሰገኑ ላንተ ሰገዱ ክብርንም ሰጡ ታላቁ ስምህ ባሸናፊነት በምድር ገነነ በድል ነሺነት
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection