Song Lyrics

የእግዚአብሔር ክንድ

ረዓብን የቆረጥክ አንተ አይደለህም ወይ ዘንዶውን የወጋህ " " " ባህሩን የከፈልክ " " " ሕዝብህን ያሻገርክ " " " አላረጀህ ጌታ በፍጹም አልደከምክ ዛሬም ይቻልሃል ሁሉንም ለማድረግ በእሳትህ መልስ ሰማያትን ቀደህ እጅጉን ናፍቀናል እስኪገለጥ ኃይልህ የእግዚአብሔር ክንድ ተነስ/3/ ኃይልን ልበስ በታላቅ ኃይል ተነስ/2/ እንደ ጥንቱ ተነስ ማስተዋልህ ታላቅ አንተ አይደለህም ወይ? ጥበብህም ግሩም " " " ዘመንህ የማያልቅ " " " ከቶ ማትለወጥ " " " ለደካማው ኃይልን ብርታት ትሰጣለህ የወደቀ አይቀርም አንተ ታነሳለህ እባክህ አምላኬ የዛለው ይበርታ መፍገምገም ይብቃና ተሃድሶን አምጣ የእግዚአብሔር ክንድ . . . መቃብር የከፈትክ አንተ አይደለህም ወይ ሞትንም ያሸነፍክ " " " ለሕዝብህ የምትራራ " " " ተዓምር የምትሠራ " " " ልጆችህ በፊትህ ክብርህን ተጠምተን አንተን እንጠራለን ይኸው ልመናችን እንየው ክንድህን በኃይል ሲንቀሳቀስ ዕውሩን ሲያበራ ድውይውን ሲፈውስ የእግዚአብሔር ክንድ . . . ሰምተህ የምትመልስ አንተ አይደለህም ወይ? ደርሠህ የምታድን " " " እስራት የምትቆርጥ " " " አርነት የምትሠጥ " " " ብዙ እንቆቅልሽ አለ በምድራችን ዘንበል እስከምትል እንጠብቅሃለን ስለ ስምህ ስትል እባክህን ጎብኘን እንደ ጥንቱ ተነስ ኃይልህን አሳየን የእግዚአብሔር ክንድ . . .
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection