በዙሪያዬ ከቦኝ ጨለማው ኢየሱስ ሲመጣ ብርሃን አየሁ ሁሉ በእርሱ ለኔ ሆኖልኛል ስሙ ይክበር ዛሬ አክብሮኛል አምላኬ መታመኛዬ ነው /2 እመሰክራለሁ በዓይኔ ስላየሁ የጠራኝ አምላክ የታመነ ነው አሃሃ/3 ፊት አይቶ አያዳላም በቅን ፈራጅ ነው/3 የውስጤን ችግር ሳልነግረው ያውቃል የልቤን ሀሳብ ፈጥኖ ይረዳል 2 አይቻለሁ /3/ በሕይወቴ በመከራዬ ቀን ደርሶልኝ ረዳቴ ጸሎቴን ሰምቶ መቼ ዝም አለኝ ድምፄን ሳሰማው እነሆኝ አለኝ 2 አላፈርኩም ስሙን ጠርቼ አላጣሁም ጌታን ተጠግቼ አይቻለሁ እኔ በሕይወቴ እመሰክራለሁ ባንደበቴ.....አምላኬ.... አምላኬን ታምኜ እወጣለሁ የሚያሰጋኝ የለም እኖራለሁ ስንቱን ቅጥር በርሱ ዘልያለሁ ከጠላቴ ወጥመድ አምልጫለሁ አቤቱ ታድጎኛል/3/ ከአዳኝ ወጥመድ እርሱ አስመልጦኛል 2 በጓዳቸው ሆነው ለሚጠሩት አይቶ ይራራል ወደ እርሱ ለጮሁት የሚሰማ አምላክ ፈጥኖ ሚደርስ ወዳጅ የለም ሌላ እንደ ኢየሱስ...... አይቻለሁ