እግዚአብሔር መልካም ነህ በመከራ ቀን መሸሸጊያ የማምለጫ ዓለት ስምህ የጸና ግንብ መጠለያ ሃሌ ሉያ/2 የዘላለም አምላክ ጌታ መኖሪያዬ በሞት ጥላም ብሄድ ውዴ መከታዬ ምድር ብትናወጥ አሃሃ ቀኝህ ደጋፊዬ እግዚአብሔር አንተ ነህ ጥላ ከለላዬ አንተ ካለህልኝ ለምን እፈራለሁ ከጥላህም በታች እተማመናለሁ ጠላትም ቢነሳ አሃሃ መቼ ያገኘኛል እግዚአብሔር አንተ እኔን ተቤዥተኸኛል የረድኤቴ ጋሻ የከፍታዬ ሰይፍ በጦርነት ብርቱ ኃይለኛ ነህ በሰልፍ አምላኬ ጉልበቴ አሃሃ መታመኛ ዓለቴ ስትዋጋ አየሁህ ቀድመኸኝ ጌታ አንተ ከፊቴ ባንተ የተወደደ ተማምኖ ይኖራል በትከሻህም ላይ በሰላምም ያርፋል እንደ ብሖር እግሮች አሃሃ ደግሞም ይበረታል