Song Lyrics

አምላኬ ሆይ

አምላኬ ሆይ እንዳንተ ያለ ማነው(3) || 2 ሲጠሩህ ፈጥነህ የምትደርስ እንባንም ከዓይን የምታብስ ጌታ ኢየሱስ አዎ ጌታ ኢየሱስ 2 አንተ ነህ ጌታ ኢየሱስ ገና ኃጢአተኛ ሳለሁ ወደኸኛል ነፍስህንም አሳልፈህ ሰጥተኸኛል በሞትህ ሕይወት አግኝቻለሁ ተባረክ ልጅህ ሆኛለሁ መለኪያ በሌለው በፍቅርህ ብዛት ከሲዖልም ታድገህ ነፍሴን ስላዳንካት ጌታዬ አከብርሃለሁ አምልኮዬን አቀርባለሁ እንደ ዋልክልኝ እንደ አንተ ውለታማ ምስጋናህን የምገልፅበት ያንሰኛል ዜማ በሙሉ ኃይሌ ዘምራለሁ በዙፋንህ ስር እሰግዳለሁ ሃሌ ሉያ /3 ውለታህ በዛብኝ ጌታ ኢየሱስ ውለታህ በዛብኝ ውለታህ በዛብኝ መድኃኒቴ ውለታህ በዛብኝ ነፍሴ ታክብርህ መድኃኒቴ ሆይ ነፍሴ ታክብርህ/2 አምልኮዬ ዝማሬዬ እልልታዬና ሽብሸባዬ ዙፋንህን ያውደው ኦሆሆ ጌታዬ 2 ለውለታህ ሌላ ምንም ስለሌለኝ አምላኬ በፊትህ እሰግዳለሁ እኔ ተንበርክኬ 2
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection