Song Lyrics

ዘሩባቤል

ዘሩባቤል ሆይ ይሄ ተራራ ከፊትህ ይጠፋል ደልዳላ ሜዳ ይሆንልሃል ሕዝቤ/2 ሆይ ይሄ ተራራ ከፊትህ ይጠፋል ደልዳላ ሜዳ ይሆንልሃል የቤቱን ስራ የጀመረው እጅህ ይጨርሰዋል ሂድ በርታ አይዞህ ለስራው የሚያበረታህን ኃይል ብርታት ጉልበትን እሰጥሃለሁኝ/2 አይቻልም ብለህ አታመንታ ቅጥሩ እንደሆነ ባንተ ያልቃል በርታ ይሄ በኔ ዓይን እጅግ ቀላል ነው ተናግሬአለሁ አደርገዋለሁ/2/ የጭንቅ የኅዘን ዘመን ይወገዳል በምስጋናዬ አፍህ ይሞላል እኔ ብቻ ነኝ ያለሁ የምኖር የጠራሁትን ሕዝቤን ማከብር/2/ በከፍታ ላይ በድል ትቆማለህ እንባህ ታብሶ ትዘምራለህ ያኔ አቅንተህ እኔን ታያለህ ያከበርኩህን ታከብረኛለህ/2/
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection