በሰማያት ካለው ከክብር ዙፋኔ ክብሬን ሁሉ ትቼ መውረዴ እኔ አምላክ ሆኜ ሳለሁ ከበረት ማደሬ ለአንተ አይደለም ወይ እንዲህ መዋረዴ አዝ፦ ተው ተመለስ ልጄ ወደ ቀድሞው ስፍራህ እባክህ አድምጠኝ ቆሜ ስጣራ ዓይኔ እያየችህ ወደ ሞት ስትሄድ አንጀቴ ታወከች ለእሳት ስትሟገት ተው ተመለስ ልጄ ወደ ቀድሞው ስፍራህ የጭንቄ ተካፋይ አጋዥም ሳይኖረኝ የሞት ጣርም ይዞኝ የደም ላብ ሲያልበኝ ይህን መከራዬን እንዴት እረሳኸው ፊትህን አዙረህ እኔን የከዳኸው አዝ፦ ተው ተመለስ ልጄ ወደ ቀድሞው ስፍራህ እባክህ አድምጠኝ ቆሜ ስጣራ ዓይኔ እያየችህ ወደ ሞት ስትሄድ አንጀቴ ታወከች ለእሳት ስትሟገት ተው ተመለስ ልጄ ወደ ቀድሞው ስፍራህ በጅራፍ ስገረፍ ሥጋዬም ሲቆረስ በጦር ተወግቼ ደሜ እንደውኃ ሲፈስ የሾህ አክሊል ጭኜ መስቀል ላይ መሞቴ እባክህ ይሰማህ ይህ ለማን ነው ልጄ አዝ፦ ተው ተመለስ ልጄ ወደ ቀድሞው ስፍራህ እባክህ አድምጠኝ ቆሜ ስጣራ ዓይኔ እያየችህ ወደ ሞት ስትሄድ አንጀቴ ታወከች ለእሳት ስትሟገት