በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው። ይላል የእግዚአብሔር ቃል። ታዲያ አንድ ማለዳ በእግዚአብሔር ፊት ሳለሁኝ ጌታን በውስጤ የተሞሉትን ጥያቄዎች ለመጠየቅ እየተዘጋጀሁኝ እንደዚህ እያልኩት ነበረ። እነዚህን ጥያቄዎች በዝማሬ እነግራቹሃለሁ በመጀመሪያም እንደዚህ ስል ጠየኩት። አዝ፦ አባባ አባ አባባ (2x) የልጅህን ጩኸት ስማ (2x) ጌታም እንደዚህ ሲል በአባትነት ፍቅር ይናገረኝ ጀመረ ልጄ እኔም እሰማሃለሁ ሳትጠይቀኝ እረዳለሁ ብረሳህ ቀኜ ትርሳኝ ብተውህ አያስችለኝም አንዳንዴ ስለምንህ አትሰማኝም ስጠይቅህ ቶሎ አትሰጠኝም ለምንድነው አባ ምትከለክለኝ እጅህን ሰብስበህ ዝም የምትለኝ ጌታም እንደዚህ ሲል በሚያባብል ቃሎቹ ይናገረኝ ጀመረ ልጄ መች ሁሉ ይጠቅምሃል አንዳንዱ እኮ ይጐዳሃል አንተ ስለማታውቀው ነዉ መች መሰለህ አምሮህ ብታየው ስከለክልህ አይክፋህ አትፍጠን ቶሎ ለኩርፊያ ጠላት ይህንን አይቶ በኩርፊያህ ደስ አታሰኘው እንደሳሙኤል አባ እኔንም ጥራኝ ድምጽህን ለይተህ አሳውቀኝ የኤሊ ድምጽማ መቼ ይጠቅመኛል እንደራሱ ልጆች ያበላሸኛል አቤት ይሄ ጌታ በፍቅር መናገር ሲችል እንደዚህ ሲል ተናገረ ልጄ ለሰዎች ድምጽማ እኔ መች እተውሃለሁ እንደ መልካም እርሻ ሁሌ እኮተኩትሃለሁ የጽድቅ ቡካያዬ ነህ ፍሬህን አበዛዋለው ዘርህን እንደከዋክብት ምድርን እሞላታለሁ አዝ፦ አባባ አባ አባባ (2x) የልጅህን ጩኸት ስማ (2x) ጌታም እንደዚህ ሲል በአባትነት ፍቅር ይናገረኝ ጀመረ ልጄ እኔም እሰማሃለሁ ሳትጠይቀኝ እረዳለሁ ብረሳህ ቀኜ ትርሳኝ ብተውህ አያስችለኝም የኤልዛቤል ዛቻ አስፈርቶኝ ከክትክታው ዛፍ ስር ወድቂያለሁኝ ረሃቡ ጸንቶብኝ ቶሎ ሳይገድለኝ አባ በጊዜ ና ቶሎ መግበኝ ጌታም በፍቅር ቃሎቹ እየደጋገመ ይናገረኝ ቀጠለ ከሰማይ መልአኬን ልኬ ልጄ እኔ እመግብሃለሁ ሁሉ የሞላኝ አባትህ እኔ ለአንተ መቼ እሰጥህሃለሁ ዳቦ ስትለምነኝ ድንጋይ ዓሣ ስትለምን እባብን እኔ መች እሰጥሃለሁ ልጄ አንተን የሚጐዳህን ከእናቴ ማህፀን መርጠህ የለየኸኝ ሰልችተህ ጣል ጣል ተው አታድርገኝ አንተ የጣልከኝ እለት ጉዴ ይፈላል ያለ አንተስ እኔ መች ያምርብኛል የፍቅር ቃሎች የሞሉት ጌታ ደግሞ እንደዚህ ብሎ ተናገረኝ እናት እንኳ ልጇን ረስታ ምናልባት ትጥል ይሆናል ልጄ እኔ ግን አልረሳህም ያለ አንተ እኮ አይሆንልኝም እጅና እግሬ የቆሰለልህ የደሜ ካሳ የሆነህ ልጄ ልጥልህ ባስብም አንጀቴ እኮ አይችልልኝም አዝ፦ የምትወደኝ አባባ (2x) ምሥጋናዬ ቤትክን ይሙላው ዕልልታዬ ቤትክን ይሙላው ምሥጋና ልቤን በሞላው ጊዜ ጌታም እንደዚህ እያለ መናገር ጀመረ ልጄ ፈጥኜ እመጣለሁ ከእኔ ጋር አኖርሃለሁ እምባ ያራሰው ፊትህን ያኔ እኔ አብሳለሁኝ አዝ፦ የምትወደኝ አባባ (2x) ምሥጋናዬ ቤትክን ይሙላው ዕልልታዬ ቤትክን ይሙላው