Song Lyrics

ክበር ንገሥ

Girum Tadesse
Kelibe Yefeleke
አዝ፦ ክበር ንገሥ ጌታ ክበር ንገሥ ክበር ንገሥ ኢየሱስ ክበር ንገሥ እንደአንተ በሰማይም የለም እንደአንተ በምድርም የለም (2x) ዘንዶውን የወጋ ረሃብን የቆራረጥክ (ክበር ንገሥ ጌታ ክበር ንገሥ) ከሃያላን በላይ ከፍ ብለህ ያለህ (ክበር ንገሥ ጌታ ክበር ንገሥ) ቅባቴን አብዝተህ ቀንበሬን (ክበር ንገሥ ጌታ ክበር ንገሥ) በቀኝ አስቀምጠህ ምስኪኑን የባረክ (ክበር ንገሥ ጌታ ክበር ንገሥ) አዝ፦ ክበር ንገሥ ጌታ ክበር ንገሥ ክበር ንገሥ ኢየሱስ ክበር ንገሥ እንደአንተ በሰማይም የለም እንደአንተ በምድርም የለም (2x) ጥቃታችን አይቶ ከቶ ዝም አይልም (ክበር ንገሥ ጌታ ክበር ንገሥ) ጠላታችን ላይ ይወጣል በበቀል (ክበር ንገሥ ጌታ ክበር ንገሥ) ከዙፋን ተነስቶ ሰይፉን ከመዘዘ (ክበር ንገሥ ጌታ ክበር ንገሥ) እንደአምላካችን ሃይለእኛ የታለ (ክበር ንገሥ ጌታ ክበር ንገሥ) አዝ፦ ክበር ንገሥ ጌታ ክበር ንገሥ ክበር ንገሥ ኢየሱስ ክበር ንገሥ እንደአንተ በሰማይም የለም እንደአንተ በምድርም የለም (2x) በግዙፍ ሰውነት በፊትህ ቢቆሙ (ክበር ንገሥ ጌታ ክበር ንገሥ) እንደነጐልያድ ታጥቀው ቢፎክሩ (ክበር ንገሥ ጌታ ክበር ንገሥ) ያልተገረዘ ፍልስጤማዊ ሰው (ክበር ንገሥ ጌታ ክበር ንገሥ) በስምህ ወንጭፌ አዋርደዋለሁ (ክበር ንገሥ ጌታ ክበር ንገሥ) አዝ፦ ክበር ንገሥ ጌታ ክበር ንገሥ ክበር ንገሥ ኢየሱስ ክበር ንገሥ እንደአንተ በሰማይም የለም እንደአንተ በምድርም የለም (2x) ማዕበሉን በስልጣን ጸጥ የሚያሰኘው (ክበር ንገሥ ጌታ ክበር ንገሥ) ደግምም በባሕር ላይ የሚመላለሰው (ክበር ንገሥ ጌታ ክበር ንገሥ) ሽማውን እንዴምቦሳ የምታዘልለው (ክበር ንገሥ ጌታ ክበር ንገሥ) ኧረ እንደአንተ ጌታ የሚችልስ ማነው (ክበር ንገሥ ጌታ ክበር ንገሥ) አዝ፦ ክበር ንገሥ ጌታ ክበር ንገሥ ክበር ንገሥ ኢየሱስ ክበር ንገሥ እንደአንተ በሰማይም የለም እንደአንተ በምድርም የለም (2x) ድምጽህ እንደነጐድጓድ ዐይኑ ነበልባል ነው (ክበር ንገሥ ጌታ ክበር ንገሥ) በሰባቱ መቅረዝ የሚመላለሰው (ክበር ንገሥ ጌታ ክበር ንገሥ) የይሁዳ አንበሳ ኢየሱስ ጌታ ነው (ክበር ንገሥ ጌታ ክበር ንገሥ) ጥንትም ለዘለዓለም ዙፋኑ ጽኑ ነው (ክበር ንገሥ ጌታ ክበር ንገሥ) አዝ፦ ክበር ንገሥ ጌታ ክበር ንገሥ ክበር ንገሥ ኢየሱስ ክበር ንገሥ እንደአንተ በሰማይም የለም እንደአንተ በምድርም የለም (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection