አዝ፦ መድሃኒቴ ብዙ ብዙ ነው ለእኔ ያረገው (ያረገው) እንደገና ስሙን ላክብረው ውለታው ለእኔ ብዙ ነው (2x) ሰው ወዳጁን ቢወድ ለጥቂቱ ነው ጥቅሙም ሲቀር ፍቅሩም ቀሪ ነው እኔ ግን ጠላትህ ሳለሁ ወደድከኝ በዘለዓለም ፍቅርህ ኢየሱስ አሰብከኝ አዝ፦ መድሃኒቴ ብዙ ብዙ ነው ለእኔ ያረገው (ያረገው) እንደገና ስሙን ላክብረው ውለታው ለእኔ ብዙ ነው (2x) መንገድ ላይ ወድቄ ጠላቴ አቁስሎኝ ማንም አልነበረም ከውድቀት ያነሳኝ ዘይትን አፍሦ ቁስሎቼን የቀባኝ እንደ ኢየሱሴ የለኝም አዳኝ አዝ፦ መድሃኒቴ ብዙ ብዙ ነው ለእኔ ያረገው (ያረገው) እንደገና ስሙን ላክብረው ውለታው ለእኔ ብዙ ነው (2x) ድካም ችግሬን የምጽሀፍንልኝ ንጉሥ ድጋፌም ጋሻም የሆንከኝ ከእናት ከአባቴም የምትበልጥብኝ መድሃኔቴ ሆይ ከፍ በልልኝ አዝ፦ መድሃኒቴ ብዙ ብዙ ነው ለእኔ ያረገው (ያረገው) እንደገና ስሙን ላክብረው ውለታው ለእኔ ብዙ ነው (2x) አንድ ሁለት ብዬ ቁጥር ብሰጠው ጌታ ውለታህ ከልክ በላይ ነው እንደ እኔ ውለታው የበዛባችሁ እኔን ተቀኙለት እልል ብላቹህ አዝ፦ መድሃኒቴ ብዙ ብዙ ነው (ብዙ ብዙ ነው) ለእኔ ያረገው (ያረገው) እንደገና ስሙን ላክብረው (ስሙን ላክብረው) ውለታው ለእኔ ብዙ ነው (ለእኔ ብዙ ነው) (2x) ዕልልታ!