አዝ፦ እግዚአብሔር ትቶኛል ለምን ትይኛለሽ የመከራሽን ቀን ማነው ያሳለፈሽ ለአንቺ የማላስብ ጨካኝ አይደለሁም ዝም ብልሽ እንኳን ቢሆን አልረሳሽም ለአንቼ የገባሁትን የተስፋ ቃሌን ምነው በጥቂቱ ተጠራጠርሺኝ በሃዘን አልቅሰሽ ለምን አስጨነቅሺኝ ስለምንስ ልጄ ጌታ ረሳኝ አልሺኝ አዝ፦ እግዚአብሔር ትቶኛል ለምን ትይኛለሽ የመከራሽን ቀን ማነው ያሳለፈሽ ለአንቺ የማላስብ ጨካኝ አይደለሁም ዝም ብልሽ እንኳን ቢሆን አልረሳሽም የሚያጽናናኝ የለም መንገድ ዳር ጥሎኛል እግዚአብሔር እንደሰው ፊቱን ከእኔ አዙሯል ተለዋዋጭ አምላክ እንደሰው ሆነብኝ ብለሽ አምተሽኛል ጌታዬ እንኳን ጣለኝ አዝ፦ እግዚአብሔር ትቶኛል ለምን ትይኛለሽ የመከራሽን ቀን ማነው ያሳለፈሽ ለአንቺ የማላስብ ጨካኝ አይደለሁም ዝም ብልሽ እንኳን ቢሆን አልረሳሽም በሃዘን ቀጠረኝ በድካም ከበበኝ ፍርዴን አጣመመው ምድረ በዳ ተወኝ በሙላት ከቤቴ ወደ እርሱ መጣሁኝ ባዶዬን አስቀረኝ ስለምንስ አልሽኝ አዝ፦ እግዚአብሔር ትቶኛል ለምን ትይኛለሽ የመከራሽን ቀን ማነው ያሳለፈሽ ለአንቺ የማላስብ ጨካኝ አይደለሁም ዝም ብልሽ እንኳን ቢሆን አልረሳሽም ጉድጓድ እንድትገቢ ጠላት ከማሰልሽ ከእሳት አውጥቼሽ ከመቼው ተረሳሽ እስቲ መለሽ ብለሽ ባርኮጽህን ቁተሪ እባክሽን ልጄ እንዲህ አታምርሪ አዝ፦ እግዚአብሔር ትቶኛል ለምን ትይኛለሽ የመከራሽን ቀን ማነው ያሳለፈሽ ለአንቺ የማላስብ ጨካኝ አይደለሁም ዝም ብልሽ እንኳን ቢሆን አልረሳሽም አጭር ዝምታዬ ነው ወይ ያስመረረሽ ጭር ያለው በረሃ ያጣልኩ ያስመሰለሽ በክረምቱ ዝናብ እረሰርስሻለሁ ያስጨነቀሽንም ሁሉ ገስጻለሁ አዝ፦ እግዚአብሔር ትቶኛል ለምን ትይኛለሽ የመከራሽን ቀን ማነው ያሳለፈሽ ለአንቺ የማላስብ ጨካኝ አይደለሁም ዝም ብልሽ እንኳን ቢሆን አልረሳሽም እስቲ አመስግኒኝ ማልቀሱን ተይና ጠላትሽን በፊቴ አሳፍሪውና በቤትሽ በጓዳሽ ሁሉ እገባና አነቃሻለሁ ዳግም እሰራሽና ተመስገን ኢየሱስ ስላሰብከን ተመስገን ጌታ ሆይ ስላየኸን ተመስገን ኢየሱስ ስላሰብከን