Song Lyrics

በዘላለም ዙፋን ላይ

Girum Tadesse
Medanite Bizu Bizu New
አዝ፦ በዘላለም ዙፋን ላይ ተቀምጠህ ያለህ በሰማይም በምድርም ሙሉ ስልጣን ያለህ ዙፋንህ ተነቃንቆ ተገርስሶ የት ያውቃል እግዚአብሔር እግዚአብሔር ነህ ዘንዶውን ገጠመክ አሸነፍክ ጌታ በኃይል በሰልፍም የምትበረታ ፅኑ ሀያላንን ሁሉ ያሸነፍክ የኃያል ኃያል ኢየሱስ ብርቱ ነህ አዝ፦ በዘላለም ዙፋን ላይ ተቀምጠህ ያለህ በሰማይም በምድርም ሙሉ ስልጣን ያለህ ዙፋንህ ተነቃንቆ ተገርስሶ የት ያውቃል እግዚአብሔር እግዚአብሔር ነህ ኃይልህ ከኃያላን ሁሉ ይበልጣል ውሀን እንደ ግንብ ቀጥ አድርጎ ያቆማል ከአጥፊዎችም እጅ ክንድህ ያስጥላል የይሁዳ አንበሳ ማን ይመስልሀል አዝ፦ በዘላለም ዙፋን ላይ ተቀምጠህ ያለህ በሰማይም በምድርም ሙሉ ስልጣን ያለህ ዙፋንህ ተነቃንቆ ተገርስሶ የት ያውቃል እግዚአብሔር እግዚአብሔር ነህ ኃይልህን ሳያውቁ የተነሱብህ አስከትተው ጦር የዘመቱብህ ክንድህ ገጥሟቸው ተሸንፈዋል ሥራቸው ጠፍቶ አንተ ነግሰሀል አዝ፦ በዘላለም ዙፋን ላይ ተቀምጠህ ያለህ በሰማይም በምድርም ሙሉ ስልጣን ያለህ ዙፋንህ ተነቃንቆ ተገርስሶ የት ያውቃል እግዚአብሔር እግዚአብሔር ነህ ሰማይ ምድርን በስልጣንህ ቃል ፍጥረት አስኪደነቅ ሰርተሀቸዋል ስላልተገኘልህ ከቶ ላንተ አቻ ሥምህ ገነነ እስከ ምድር ዳርቻ አዝ፦ በዘላለም ዙፋን ላይ ተቀምጠህ ያለህ በሰማይም በምድርም ሙሉ ስልጣን ያለህ ዙፋንህ ተነቃንቆ ተገርስሶ የት ያውቃል እግዚአብሔር እግዚአብሔር ነህ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection