Song Lyrics

ምሥጋና ይሁን

Girum Tadesse
Medanite Bizu Bizu New
አዝ፦ ምሥጋና ይሁን ምሥጋና ምሥጋና ለእርሱ ምሥጋና ይዘመናቱ የታሪክ ጌታ የእኛ ኢየሱስ የማይረታ (2x) ብዙ ብርቱዎች በምድር ነበሩ ሊገዳደሩ ፍፁም የጣሩ ስራቸው ሁሉ እንደጉም በኗል አንተ ግን ጌታ ዛሬም ከብረሃል አዝ፦ ምሥጋና ይሁን ምሥጋና ምሥጋና ለእርሱ ምሥጋና ይዘመናቱ የታሪክ ጌታ የእኛ ኢየሱስ የማይረታ (2x) በዘመናት ውስጥ የተቋቋመህ ከቶ ማን ነበር አንተን የረታህ ትጥቅህ ጠንካራ ብርቱ ሰልፈኛ የእኛ ኢየሱስ ታላቅ ጦረኛ አዝ፦ ምሥጋና ይሁን ምሥጋና ምሥጋና ለእርሱ ምሥጋና ይዘመናቱ የታሪክ ጌታ የእኛ ኢየሱስ የማይረታ (2x) በምድር በሰማይ ይህ ሥልጣን ያለህ ፍጥረታት ሁሉ የሚሰግዱልህ ሞገስህ ትልቅ ወሰን የሌለው የእስራኤል ቅዱስ ሚመስልህ ማነው አዝ፦ ምሥጋና ይሁን ምሥጋና ምሥጋና ለእርሱ ምሥጋና ይዘመናቱ የታሪክ ጌታ የእኛ ኢየሱስ የማይረታ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection