Song Lyrics

አንድ ነገር የምፈራው

Girum Tadesse
Kelibe Yefeleke
አዝ፦ አንድ ነገር በሕይወቴ የምፈራው አንተ ዝም ስትለኝ ነው (2x) አንድ ነገር በሕይወቴ የምሰጋው አንተ ዝም ስትለኝ ነው (2x) እባክህ ተናገረኝ ኢየሱስ ዝም አትበለኝ ሁሉን ወደምትችል ወደአንተ እጮሃለሁ ልትረዳኝ እንደምትችል ይህንን አውቃለሁ በወደድከው መንገድ ጌታ ተናገረኝ ብቻ አንድ ነገር ኢየሱስ ዝም አትበለኝ ብቻ አንድ ነገር አባ ዝም አትበለኝ አዝ፦ አንድ ነገር በሕይወቴ የምፈራው አንተ ዝም ስትለኝ ነው (2x) አንድ ነገር በሕይወቴ የምሰጋው አንተ ዝም ስትለኝ ነው (2x) እባክህ ተናገረኝ ኢየሱስ ዝም አትበለኝ ሙግቴ ከአንተ ጋር መሆኑን ስታውቀው ለምን ዝም እንዳልከኝ ያልገባኝ ሚስጥር ነው ተናገረኝ ጌታ ያየኸው ጉድለቴን አንተ ዝም ካልክማ ሌላ ማነው ያለኝ አንተ ዝም ካልክማ ሌላ ማንም የለኝ አዝ፦ አንድ ነገር በሕይወቴ የምፈራው አንተ ዝም ስትለኝ ነው (2x) አንድ ነገር በሕይወቴ የምሰጋው አንተ ዝም ስትለኝ ነው (2x) እባክህ ተናገረኝ ኢየሱስ ዝም አትበለኝ አንተ ዝም ባልክበት በካህኑ ኤሊ ዘመን ድል አይታወቅም ሁሌ መሸነፍ ነው እስከ ሲዖል ድረስ ነፍስን ያወርዳታል የአንተ ዝምታ ነፍሴን ያሰጋታል (2x) አዝ፦ አንድ ነገር በሕይወቴ የምፈራው አንተ ዝም ስትለኝ ነው (2x) አንድ ነገር በሕይወቴ የምሰጋው አንተ ዝም ስትለኝ ነው (2x) እባክህ ተናገረኝ ኢየሱስ ዝም አትበለኝ መልሰህ መላልሰህ ብትናገረኝም ማስተዋል ቢያቅተኝ ተው አትሰልቸኝ በአባትነት ፍቅርህ በልምጭ ሾጥ አርገኝ ዝም ካልከኝማ አባ ዋጋም የለኝ ዝም ካልከኝማ ኢየሱስ ዋጋም የለኝ አዝ፦ አንድ ነገር በሕይወቴ የምረካው አንተ ስትናገረኝ ነው (2x) አንድ ነገር በሕይወቴ የምፈታው አንተ ስትናገረኝ ነው (2x) እባክህ ተናገረኝ እለመልማለሁ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection