መከራን ባየሁበት ምድር በገፉኝ ሰዎች ልከበር ታሪኬን ከገለበጥከው ልቤን ደስ ካሰኘኸው ምሥጋናዬን ይኸው በፊትህ እንዳከበርከኝ ላከብርህ ያለኝም ይኸው ነውና አንተው ከሰጠኸኝ ሌላ አሃሃ አንተው ከሰጠኸኝ ሌላ አዝ፦ ተመስገን ጌታ ተመስገን ተመስገን ተመስገን (2x) በምሽት በሬ ሲንኳኳ መች መሰለኝ የምትመጣ ለካ ከሩቅ ተመልክተህ አስተዳዳሬ የአላማረህ አንተው ነህ የተጠጋኸኝ አስፈሪውን ሌት ያሳለፍከኝ ከብሬን ከደጄ አፍስሰህ ጠረኔን ለወጥክ አጣፍጠህ አህህ ጠረኔን ለወጥክ አጣፍጠህ አዝ፦ ተመስገን ጌታ ተመስገን ተመስገን ተመስገን (2x) ምሥጋናዬን ከወደድከው ስሰዋውም ካሸተትከው ከቃዬል መስዋዕት ካስበለጥከው ለአንተ ስሰዋ ውላለሁ ቀጥ ብሎ ወደላይ ይውጣ አርጐ በፊትህ ጌታ ደስ የሚያሰኝህ ምሥጋና ይሽተት ማደሪያህ ይግባና አሜን ይሽተት ማደሪያህ ይግባና አዝ፦ ተመስገን ጌታ ተመስገን ተመስገን ተመስገን (2x)