ከሞት የበረታ ፍቅሩ አሽነፈኝ ነፍስም አልቀረልኝ ወድጄዋለሁኝ ሰዎች ሌላም ቢሉም ለእኔ ግን ፍቅር ነው ኢየሱስ ኢየሱስ ብዬ የማልጠግበው አዝ፦ የማልጠግበው እኔስ የማልጠግበው የማልጠግበው እኔስ ኢየሱሴን ነው (2x) በመልካምነቱ ደስታን አጠገበኝ (2x) ባርኮቱ በሞላው ድንኳኑ ያኖረኝ (2x) ሥጋት ቀርቶልኛል ተደላድያለሁ (2x) የእግዚአብሔር ልጅ ነው ከእኔ ጋራ ያለው (2x) አዝ፦ ከሰው ሁሉ ልዩ እርሱን የሚያደርገው ፍቅሩ ወረት አያውቅ ዘለዓለማዊ ነው (2x) የሚከታተለኝ በሄድኩበት ቦታ (2x) ዐይኖቹ ዐይነሱም ከእኔ ላይ ለአንድ አፍታ (2x) የገባኝ ይሄ ነው እንዲሁ ወዶኛል (2x) ፍቅሩም ከማር ይልቅ እጅግ ይጣፍጣል (2x) አዝ፦ ከወይን ጠጅ ይልቅ ፍቅሩ አጥግቦኛል እኔስ ሌላ አልሻም ኢየሱስ ይበቃኛል (2x) ያስደንቀኝ ጀመረ እየዋለ እያደር (2x) በእኔ ላይ የበዛውን ምህረቱን ስቆጥር (2x) ፍቅርና ምህረቱ ከቶ ገደብ የለው (2x) ይህን ኢየሱሴን ነፍሴ ወደደችው (2x) አዝ፦ ከወይን ጠጅ ይልቅ ፍቅሩ አጥግቦኛል እኔስ ሌላ አልሻም ኢየሱስ ይበቃኛል (2x)