እኔ ያልዘመርኩ ማን ይዘምር? ለኢየሱሴ ሥሙ ክብር ስንቴ ከሞት አምልጫለሁ? ሲታደገኝ አይቻለሁ እንደ እኔ ምሕረት የበዛለት ምሥጋናውን ይሰዋለት የታሪኬ ጅማሬና የፍጻሜ መደምደሚያው በሕይወቴ ሥፍራ ያለው አንድ ቁጥር ለኢየሱስ ነው በቁልምጫ የምጠራው ፍቅሩ ልቤን ነክቶት ነው በደም ተለውሼ ሲያየን ፊቱን ዞሮ ያላለፈኝ ጠርቶ በሕይወት ኑር ያለኝ ምሕረቱን ያበዛልኝ እንደ እኔ ማን አለና ነው? ከማመስገን የምዘገየው ይህን ጌታ አንተ አምላኬ ነህ አልኩት አምላኬ ነህ አልኩት መንገድ ዳር ወድቄ ሲያየኝ ራርቶ በፍቅር ያኖረኝ ቸርነቱ በዝቶ እስኪታይ ሰማይን ከፍቶ በእኔ ላይ ወደ ራሱ ስላስጠጋኝ እንዳልዘምር ማነው ከልካይ? ይህን ጌታ አንተ አምላኬ ነህ አልኩት አምላኬ ነህ አልኩት በዘመኔ ብዙ ነገር አይቻለሁ እግዚአብሔርን ትልቅ ነህ ብዬዋለሁ ባሕር ከፍሎ ሲያሻግረኝ ዓይኔ አይቶታል እግዚአብሔርን ትልቅ ነህ ብሎታል በዘመኔ ብዙ ነገር አይቻለሁ እግዚአብሔርን ፍቅር ነህ ብዬዋለሁ ሲሸከመኝ ሲታገሰኝ ዓይኔ አይቶታል እግዚአብሔርን ፍቅር ነህ ፍቅር ነህ ብሎታል