Song Lyrics

ክብሩ ለአንተ

Getachew Tadesse
Ene Yalzemerkugn
አዝ፦ ክብሩ ለአንተ ይሁን ጌታ መድኃኒቴ ከውስጥም ከውጭም ሰላም ሞላ ቤቴ ተመስገን ጌታዬ ከፍ አደርግሃለሁ አንተን በማግኘቴ እኔም ሰው ሆኛለሁ ስምህን እየጠራሁ እባርክሃለሁ ስንቱን በአንተ አልፌ ለዚህ ደርሻለሁ ከዓለም ወጣሁና ምን ይቀርብኛል? ይመስገን ጌታዬ ሁሉ ሞልቶልኛል በግርፋት ቁስሉ እርሱ ፈውሷታል ነፍሴም ከዚህ ውጭ ምን ያስፈልጋታል? ከዚህ የተሻለ ምን ለውጥ ሊያመጣልኝ የሚለኝ ጠላቴ ርስትህን ለውጠኝ አዝ፦ ክብሩ ለአንተ ይሁን ጌታ መድኃኒቴ ከውስጥም ከውጭም ሰላም ሞላ ቤቴ ተመስገን ጌታዬ ከፍ አደርግሃለሁ አንተን በማግኘቴ እኔም ሰው ሆኛለሁ ስምህን እየጠራሁ እባርክሃለሁ ስንቱን በአንተ አልፌ ለዚህ ደርሻለሁ ራሴን ስመለከት ለዚህ የማልበቃ እንዴት ተደባለቁ ከአንተ ቅዱስ መንጋ? ርስትህን አወረስኸኝ ከቅዱሣን ጋራ ከአንተ ጋር አኖርኸኝ ሰማያዊ ሥፍራ ምሕረትህ ደርሶኛል ለዚህ በቅቻለሁ እኔም በዘመኔ እገዛልሃለሁ አዝ፦ ክብሩ ለአንተ ይሁን ጌታ መድኃኒቴ ከውስጥም ከውጭም ሰላም ሞላ ቤቴ ተመስገን ጌታዬ ከፍ አደርግሃለሁ አንተን በማግኘቴ እኔም ሰው ሆኛለሁ ስምህን እየጠራሁ እባርክሃለሁ ስንቱን በአንተ አልፌ ለዚህ ደርሻለሁ ታስሬ አግኝተህ ነው አንተ ያስፈታኸኝ እኔም ነጻ ወጣሁ ጌታ ስላሰብኸኝ ስለ እኔ የሚጠይቅ አጭር መልስ ያገኛል ትዕዛዝን ሰጥተህ ነው ብለህ ያስፈልገኛል ክብርን አለበስኸኝ ውርደቴ ቀረና ተገረመ ሁሉም መዳኔን አየና አዝ፦ ክብሩ ለአንተ ይሁን ጌታ መድኃኒቴ ከውስጥም ከውጭም ሰላም ሞላ ቤቴ ተመስገን ጌታዬ ከፍ አደርግሃለሁ አንተን በማግኘቴ እኔም ሰው ሆኛለሁ ስምህን እየጠራሁ እባርክሃለሁ ስንቱን በአንተ አልፌ ለዚህ ደርሻለሁ የማመልክህ አምላክ ጊዜያዊ አይደለም ትላንትና የሌለህ ዓለም የማታውቅህ አይደለም ጌታዬ ታሪክ ያፈለቀህ ለዚህች ዓለም እንኳ ራስህ መድኃኒት ነህ ለጠየቀኝ ሁሉ ለመልስ ዝግጁ ነኝ ውዴ መድኃኒቴ እኔን እንዳዳንኸኝ አዝ፦ ክብሩ ለአንተ ይሁን ጌታ መድኃኒቴ ከውስጥም ከውጭም ሰላም ሞላ ቤቴ ተመስገን ጌታዬ ከፍ አደርግሃለሁ አንተን በማግኘቴ እኔም ሰው ሆኛለሁ ስምህን እየጠራሁ እባርክሃለሁ ስንቱን በአንተ አልፌ ለዚህ ደርሻለሁ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection