Song Lyrics

ከምልህ በላይ ነህ

Getachew Tadesse
Ene Yalzemerkugn
ኤልሻዳይ ብዬ ዘምሬአለሁ ጌታም ነህ ብዬ መስክሬአለሁ አሁን ግን ቃላትን ስላጣሁ ከምለው በላይ ነህ ብያለሁ ከምልህ በላይ ጌታ (3x) ነህ የእኔ ቃላት የማይገልጽህ የሰው ቃላት ከምልህ በላይ ጌታ ነህ እኔን አሳፍሮኝ አያውቅም የማገለግለው ጌታ ያኖረኛል በምድር ላይ ጠላቶቼን እየመታ ለምን ይህን አደረግህ? ብሎ የጠየቀው የለም ሥልጣኑ ከሁሉ በላይ ጉልበቱ ኤልሻዳይ ነው እሠይ (6x) ጌታ ነው በምድር በሰማይ ከሁሉም በላይ ነው ኢየሱስ በምድር በሰማይ ከሁሉም በላይ ስለ በደሌ ዝቅ ብሎ መስቀል ተሸክም ያየው ሰው የሰማይ የምድር ጌታ ነው ብሎ ማን ይገምተው? ቢሆንም ተነሥቶ ጌታ በዓብ ቀኝ ተቀምጧል በሰማይና በምድር ሁሉን አንበርክኳል ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን ራስ ሆነ አይጠቅምም ብለው የጣሉት የትንሣዔ ጌታ ሆነ የናቁትን አሳፍሮ እጅ አስጭኗቸዋል በመንግሥቱም እያበራ ዘለዓለም ይኖራል
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection