Song Lyrics

አንድን ነገር

Getachew Tadesse
Ene Yalzemerkugn
አዝ፦ እግዚአብሔርን አንድን ነገር ለምኜዋለሁ ያንን ከእጁ እናፍቃለሁ አሮጌውን በአዲስ ተክቶ እስኪወስደኝ ጌታዬ መጥቶ የሞተልኝ ወዳጄን እስካይ ናፍቆቴ እስኪፈጸም በሰማይ እንዲጠብቀኝ ምድር ላይ አዝ፦ እግዚአብሔርን አንድን ነገር ለምኜዋለሁ ያንን ከእጁ እናፍቃለሁ በሕይወቴ ዘመን በሙሉ ልኖር እኔም እንደ ሕያው ቃሉ ምኞቴ ነው ይህ አንድ ነገር እስካለሁ በዚህች ጠፊ ምድር ይህን ነገር እናፍቃለሁ አዝ፦ እግዚአብሔርን አንድን ነገር ለምኜዋለሁ ያንን ከእጁ እናፍቃለሁ የመምጫህን ቀን ስለማላውቅ ጌታ ኢየሱስ የአንተን መገለጥ ያለ ነውርና ነቀፋ ሆኜ እንድጠብቀው በተስፋ ይህን ነገር እናፍቃለሁ አዝ፦ እግዚአብሔርን አንድን ነገር ለምኜዋለሁ ያንን ከእጁ እናፍቃለሁ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection