Song Lyrics

ልዩ ነህ

Getachew Tadesse
Ene Yalzemerkugn
አንተ እኮ ለእኔ ጌታ ነህ አንተ እኮ ለእኔ ልዩ ነህ አንተ እኮ ለእኔ ወዳጄ ነህ ሥሜን በሰማዩ መዝገብ መቀመጫዬን በአብ ቀኝ እረፍትን ለዘለዓለም ለዘመኔም ቁጥር የለም ስሄድ በመላዕክት ታጅቤ እኔም በአምላኬ ታስቤ ሰማያት ደስ እያላቸው እኔ መዳኔ ገርሟቸው በትውልድ ላላገኘሁት በትምህርት በዕውቀት በችሎታ የማያልፍ ክብር አውራሼ ልዩ ነህ ለእኔ የእኔ ጌታ ልዩ ነህ ጌታ ልዩ ነህ ልዩ ነህ ኢየሱስ ለእኔስ ልዩ ነህ ስለጥበቃህ አልሰጋም ተጠብቄ አይቻለሁ ስለማዳንህ ብናገር አለኝ ብዙ አወራለሁ አባትነትህማ ለእኔ ሆኖኝ ጧት ማታ ትዝታ እኖራለሁ ተደስቼ በአንተ በአስደናቂ ጌታ በዘመድ አልታመንም ዛሬ ታይቶ በሚጠወልግ ብሩንም አይቼዋለሁ እንደ ጉድፍ ቆጥሬዋለሁ በምንም የማይገመት ሀብቴ ትምክህቴ ልዩ ኩራቴ የሕይወት ዘመን ምርጫዬ አንተ ነህ ለእኔስ ጌታዬ ማንም ላይገዛኝ ኖራለሁ ሁሉን በአንተ አሸንፌአለሁ የሚገዛኝ በዚህ ዓለም ከአንተ ውጭ ማንም የለም ገንዘብ ሀብት ዕውቀት ንብረት በዚህ ዓለም ነገር መጠመድ አበቃ አከተመለት ከአንተ የተገናኘን ዕለት
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection