አዝ፦ ጠላቴ ሆይ ስማኝ ዛሬም እነግርሃለሁኝ ብወድቅ እነሣለሁኝ በጨለማ ብቀመጥም እንኳን እግዚአብሔር ብርሃን ይሆንልኛል እርሱ ወጥመድህን ይቆርጥልኛል አይምሰልህ ለዘለዓለም አምላኬ ማንንም አይጥልም ለዘለዓለም አምላኬ ማንንም አይጥልም በድካሜ የሚራራልኝ የእግዚአብሔር ልጅ ስላለልኝ ወደ ብርሃን ያወጣል ክብሩን በግልጽ ያሳየኛል ሁለቴም ባይንሽ ታያለሽ በዕፍረት ትከደኛለሽ ትረገጭ እንደ ጭቃ ይህ ሊሆን ግድ ነው በቃ አዝ፦ ጠላቴ ሆይ ስማኝ ዛሬም እነግርሃለሁኝ ብወድቅ እነሣለሁኝ በጨለማ ብቀመጥም እንኳን እግዚአብሔር ብርሃን ይሆንልኛል እርሱ ወጥመድህን ይቆርጥልኛል አይምሰልህ ለዘለዓለም አምላኬ ማንንም አይጥልም ለዘለዓለም አምላኬ ማንንም አይጥልም ሙሴ እናቱ ስትጥለው የምታደርገው ነገር ጠፍቶ መወሸቂያ መደበቂያ የሚሆን ሥፍራ ለርሱ ታጥቶ እግዚአብሔር ግን ተቀበለው ከእጇ ሥር ወስዶ አቀፈው የተፈራ ቤት ሊያኖረው ክብሩን በግል እያሳየው አዝ፦ ጠላቴ ሆይ ስማኝ ዛሬም እነግርሃለሁኝ ብወድቅ እነሣለሁኝ በጨለማ ብቀመጥም እንኳን እግዚአብሔር ብርሃን ይሆንልኛል እርሱ ወጥመድህን ይቆርጥልኛል አይምሰልህ ለዘለዓለም አምላኬ ማንንም አይጥልም ለዘለዓለም አምላኬ ማንንም አይጥልም መች ይጥላል የእኔ ጌታ? ያነሣል ወደ ከፍታ ለጠበቀው ለታገሰው የሚያኮራ ምላሽ አለው አዝ፦ ጠላቴ ሆይ ስማኝ ዛሬም እነግርሃለሁኝ ብወድቅ እነሣለሁኝ በጨለማ ብቀመጥም እንኳን እግዚአብሔር ብርሃን ይሆንልኛል እርሱ ወጥመድህን ይቆርጥልኛል አይምሰልህ ለዘለዓለም አምላኬ ማንንም አይጥልም ለዘለዓለም አምላኬ ማንንም አይጥልም