አዝ፦ ድንቅ ነህ (4x) ኢየሱስ ልዩ ነህ ሃሌሉያ አሃ ሃ ድንቅ ነህ (4x) ለእኔ ክብር ነህ አስደናቂነትህን አይተን እስከዛሬ እንጂ መቼ ኖርን? ሰምተን ጭፍን ወሬ ሥራህን በሕይወታችን ተገልጦ ስላየነው አናፍርም ያኮራል የአንተ መሆን ክብር ነው አዝ፦ ድንቅ ነህ (4x) ኢየሱስ ልዩ ነህ ሃሌሉያ አሃ ሃ ድንቅ ነህ (4x) ለእኔ ክብር ነህ ቃላት አጣሁ እንጂ ብዙ እናገር ነበር ጠላት በእኔ ዘግቶ ስለከፈትክልኝ በር ርስት አገኘሁ እንጂ መች በዚህ አበቃ? በቤትህ ወግ አየሁ ቀረና ሰቆቃ አዝ፦ ድንቅ ነህ (4x) ኢየሱስ ልዩ ነህ ሃሌሉያ አሃ ሃ ድንቅ ነህ (4x) ለእኔ ክብር ነህ ለእኔ አጋዥ የሚሆን ጠፍቶ ዝም ሲባል ረዳቴ ሆነኸኝ ከተፍ ብለሃል የቀራንዮ ወዳጅ ተባረክ ዘለዓለም የክፉ ቀን ወዳጅ እንዳንተ ያለ የለም አዝ፦ ድንቅ ነህ (4x) ኢየሱስ ልዩ ነህ ሃሌሉያ አሃ ሃ ድንቅ ነህ (4x) ለእኔ ክብር ነህ