Song Lyrics

ትልቅን ነገር አስባለሁ

Feben Demissie
Selfu Yegziabher New
በማዘን መተከዝ እግዚአብሔር ይከብር ይመስል ምንድን ነው መርበትበት ሁልጊዜ መቆዘም ጠላት ነው እንጂ በዚያ ደስ ደስ የሚለው ምን ይጨምራል የአምላክን ሃይል መጠርጠር ነው አዝ፦ አላንጐራጉርም አንገቴንም አልደፋም እግዚአብሔር እንቅቶኛል ጊዜዬን አላጠፋም (2x) ምን አሸማቀቀኝ ምን አንገቴን አስደፋኝ ጌታዬ ከእኔ ጋር ሆኖ እያየሁኝ የማልፍበት ሁሉ እንደምናምን ቢመስልም ነጥሬ እወጣለሁ ወደኋላዬ አልልም አዝ፦ አላንጐራጉርም አንገቴንም አልደፋም እግዚአብሔር እንቅቶኛል ጊዜዬን አላጠፋም (2x) የትም ስፍራ ብሆን የሚይዘኝ ምንም የለም እሰራለሁ ስራ አለኝ ገና ያልጀመርኩት ሲያየኝ ጠላቴ ለዐይኑ ባልሞላለትም እግሬ የረገጠበት ሰላም አልሰጠውም አዝ፦ አላንጐራጉርም አንገቴንም አልደፋም እግዚአብሔር እንቅቶኛል ጊዜዬን አላጠፋም (2x) የደከምኩ ስመስለው አሳድደዋለሁ ተኛታለች ብሎ ሲል ህልምን አልማለሁ ዛሬ አዘነች ሲል እዘምራለሁ ከአምላኬ ተጣብቄ ግራ አጋባዋለሁ አዝ፦ አላንጐራጉርም አንገቴንም አልደፋም እግዚአብሔር እንቅቶኛል ጊዜዬን አላጠፋም (2x) ትልቅን ትልቅን ነገርን ሁልጊዜ አስባለሁ አምላኬ ያንኑ ሲያደርግ አየዋለሁ ከፍ ያለውን ከፍ ያለውን ነገርን ሁልጊዜ አስባለሁ አምላኬ ያንኑ ሲያደርግ አየዋለሁ (4x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection