እግዚአብሔር ምናመልክህ አስከብረኀን አይደለም ብናመልክህ ብንሰግድልህ ስለተገባህ የምትወደድ አምላክ ነህ ላወቀህ ለቀረበህ ፍቅርህ ያዘምረናል ምሥጋናህ እናመልክሃለን እግዚአብሔር አዝ፦ በሙሉ ሃይላችን በሙሉ ነፍሳችን በሙሉ ልባችን እናመልክሃለን (2x) የዘለዓለማዊው መንግሥት አምባሳደሮች ልንሆን ልትወደን ልትመርጠን አላፈርክብን ልጆቼ ብለህ ጠራኀን አባ አባት ልንልህ ፈቀድክ በድፍረት ፊትህን ልናይ ብቁ አደረግከን እናመልክሃለን እግዚአብሔር አዝ፦ በሙሉ ሃይላችን በሙሉ ነፍሳችን በሙሉ ልባችን እናመልክሃለን (2x) አባትነትህን ለማግኘት ከእኛ ምንም አላስከፈልክ ይልቁን ልጅህን ሰጥተህ ከእኛ ታረቅህ እንዴት ያለ ፍቅር ነው አንተ ለእኛ ያሳየኀው ለአንተ መኖር መስገድ መቀኘት ሲያንስህ ነው አዝ፦ በሙሉ ሃይላችን በሙሉ ነፍሳችን በሙሉ ልባችን እናመልክሃለን (3x) በሙሉ ልባችን እናመልክሃለን (5x)